2015

You might also like

Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 46

ደቡብ ምዕ/ ኢት/ሕ/ክ መንግስት

ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

በሕዝብ ክንፍ ሚና፣ አደረጃጀት፣ አሠራርና የምዘና ሥርዓት

ማኑዋል ዙሪያ

ለዞን መምሪያ ኃላፎዎች፤ባለሙያዎች እና የቢሮአችን


ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተዘጋጀ ሥልጠና

ግንቦት/2015 ዓ.ም
ቦንጋ
የህዝብ ክንፍ ምንነት
 የህዝብ ክንፍ፡- ማለት የቆመለትን የህብረተሰብ ክፍል መብትና ጥቅም
ለማስከበር አደረጃጀቱን ወክሎ ከተቋማት ጋራ የሚሰራ በተለያየ ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ መሰረቶች የተደራጀ የህዝብ አካል ነው፡፡
 የህዝብ ክንፍ ተሣትፎ ግቦች

 የህዝብ ክንፉን ከዕቅድ ዝግጅት እሰከ አፈጻጸም ምዘና ሂደት በማሳተፍና አቅም
በመገንባት የመንግስት አገልግሎትን፡-
 ቅልጣፌ፣
 ውጤታማነትና
 ፍትሐዊነት እንዲሁም
 ተጠያቂነትን እና የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው፡፡
የህዝብ ክንፍ መለያ መስፈርቶች
 ተቋማት ከህዝብ ክንፉ ጋር በአጋርነት ተልዕኮአቸውን በመወጣት የበለጠ ውጤታማ
እንዲሆኑ የህዝብ ክንፋቸውን መለየት አለባቸው፡፡
 የተለያዩ የጥናት ውጤቶች እንደሚያመለክቱት ስድስት የህዝብ ተሳትፎ መለያ
መስፈርቶች ያሉ ሲሆን ይህንም በሚከተለው መልኩ ማየት ይቻላል፡፡
 ሀ. ወካይነት:- ተቋማት አገልግሎት ከሚሰጡት የህብረተሰብ ክፍል በቁጥር አብላጫ፣ በዕድሜ፣ በጾታ፣
በሥራ ሁኔታ፣ በልዩ ልዩ አደረጃጀት ወካይ የሆነውን የህዝብ ክንፍ በመለየት ማደራጀት ነው፡፡
 ለ. ተጽዕኖ የማሳደር ሁኔታ፡- ተቋማት የህዝብ ክንፋቸውን ለመምረጥ ውሳኔ ላይ ከመድረሳቸው በፊት
ለህዝብ በሚሰጡት አገልግሎት፣ ዋና ዋና ጉዳዮችና በውሳኔዎች ላይ ተገልጋዩን ህብረተሰብ በመወከል
ተጽዕኖ ሊፈጥር ይችላል የሚለውን ማየት ይኖርበታል፡፡
 ሐ. በወቅቱ መገኘት፡- በተቋማት በሚኖረው የምክክርና የውይይት ሂደት ወቅቱን የጠበቀና ዘላቂ የህዝብ
ተሳትፎ ማድረግ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
የቀጠለ---------------

 መ. ዓላማ ተጋሪ፡- ተቋማት ለህዝብ በሚሰጡት አገልግሎት የተቋሙን ዓላማና የስራ


ባህርይ መጋራትና መተባበር የሚችል ማነው የሚለውን ግምት ውስጥ ማስገባት
ያስፈልጋል፡፡
 ሠ. ተነሳሽነት ያለው:- ይህም ማለት በተቋማት የዕቅድ አፈጻጸም ሂደት እና
በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በፈቃደኝነትና በራስ ተነሳሽነት በመሳተፍ እስከ ፍጻሜ
ድረስ ያለውን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም የተሳትፎውን ቀጣይነት
ማረጋገጥ የሚችል፡፡
 ረ. መረጃ መቀበል፣ መጠቀምና መስጠት:- ህዝብ በተቋማት የውይይት መድረኮችና
በሌሎች የግንኙነት አግባቦች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የመረጃ ልውውጡ ትርጉም
እንዲኖረው መረጃ መቀበል፣ መጠቀምና መስጠት የሚችል መሆን አለበት፡፡
በህዝብ ክንፍ ልየታ ረገድ ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች

 በተቋሙ አገልግሎት አሠጣጥና በሚደረጉ ውሳኔዎች ላይ፡-

 በቀጥታ ተጠቃሚና ተጎጂ የሆነውን፣

 በተዘዋዋሪ መንገድ ተጽዕኖ የሚደርስበትን፣

 ተጽእኖ ፈጣሪ ሊሆን የሚችለውን፣

 የመጠየቅ ህጋዊ መብት ያላቸውን፣

 የሞራልና የመብት ጥሰት ጥያቄ ሊያነሱ የሚችሉትን፣

 የተለያዩ የህብተሰብ ክፍሎችን ፍላጎት ለማሳካት ወክለው መቆም የሚችሉትን፣

 ለመተግበር ኃላፊነት ሊወስዱ የሚችሉና ተነሳሽነት ያላቸውን፣

 በውይይትና በትግበራ ሂደት ተገቢ ምላሽ መስጠትና ምቹ ሁኔታ መፍጠር የሚችሉትን፣

 በትግበራ ሂደት ከመከታተል፣ መረጃ ከማሰባሰብ፣ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ከማድረግ


አንጻር ቁርጠኛ ሊሆኑ የሚችሉትን የህብረተሰብ ክፍሎችን መለየትና ማሳተፍ ናቸው፡፡
የህዝብ ክንፍ በመለየት የሚሳተፍበት አግባብ
 የህዝብ ክንፍ ልየታና ተሣትፎ በሁሉም የክልሉ መንግስት ተቋማት መተግበር
ያለበት ሲሆን የህዝብ ክንፍ ልየታው፡-
 ሀ. ህዝቡ በህገ-መንግስቱና ሌሎች ህጎች የተረጋገጡለትን ፖለቲካዊ፣
 ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መብቶች ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር፣
 ለ. ተቋሙ በተልዕኮ ከተሰጠው ኃላፊነትና ለህዝቡ እንዲያቀርብ
 ከሚጠበቅበት አገልግሎት አንጻር፣
 ሐ. የህዝቡን አቅም በመገንባት ቀጥተኛ የልማቱ ባለቤት፣ ተሣታፊና
 ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር፣
 መ. የግል ሴክተሩና የሲሰቪል ማህበረሰብ የልማቱ አጋዥ ኃይል ከማድረግ
 አንጻር መሠረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡
የህዝብ ክንፍ አደረጃጀትና አሰራር

 አደረጃጀት
 በክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ተቋማት የህዝብ ክንፋቸው እስከምን ድረስ ሊሆን
እንደሚገባው በውል ተገንዝቦ ተገቢውን የግንኙነት አግባብ ከመፍጠር አንጻር፡-
 የግልፅነትና የወጥነት ውስንነቶች ይታያሉ፡፡
 ይህም በየአስተዳደር እርከኑ እንደ መነሻ የሚያገለግል የህዝብ ክንፎች አደረጃጀትና
አሰራር አለመዘርጋቱ የፈጠረው ችግር መሆኑን በተለያዩ ጊዜአቶች በተደረገው
ክትትልና ድጋፍ ውይይቶች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
 በዚህ መነሻ በሚከተለው አግባብ የህዝብ ክንፎች አደረጃጀት ስዕላዊ መግለጫ
ተመላክቷል፡፡
የቀጠለ------------------------

ስ ዕል 1፡- ከክል ል እስ ከ ቀ በሌ ድ ረስ ያለው ን የህ ዝ ብ ክን ፍ አደረጃጀት የሚ ያሳ ይ ቻር ት

በክል ል ደረ ጃ ሊ ካተ ቱ የሚ ገቡ የህ ዝ ብ ክን ፎ ች ፡- ብዙ ሃ ን
ማ ህ በራ ት ፣ የ ሙ ያ ና ሌ ሎ ች ማ ህ በራ ት

በዞን ደረ ጃ ሊ ካተ ቱ የሚ ገቡ የህ ዝ ብ ክን ፎ ች ፡- ብዙ ሃ ን
ማ ህ በራ ት ፣ የ ሙ ያ ና ሌ ሎ ች ማ ህ በራ ት

በል ዩ ወ ረዳ፣ በወ ረዳና ከተ ማ አስ ተ ዳደር ደረ ጃ ሊ ካተ ቱ


የሚ ገቡ የህ ዝ ብ ክን ፎ ች ፡- ብዙ ሃ ን ማ ህ በራ ት ፣ የ ሙ ያ ና ሌ ሎ ች

ማ ህ በራ ት

በቀ በሌ ደረ ጃ ሊ ካተ ቱ የሚ ገቡ የህ ዝ ብ ክን ፎ ች ፡- ዜ ጋ ው /ህ ዝ ቡ
ሀ. በተልዕኳቸውና በአደረጃጀታቸው የተለዩ የሕዝብ ክንፍ አካላት

የብዙሃን ማህበራት፡-

 እንደ ሴቶችና ወጣቶች፣

 አርሶ አደሮች/አርብቶ አደሮችና

 ሌሎች የጋራ ጥቅሞቻቸውንና ፍላጎቶቻቸውን መሠረት አድርገው የተደራጁ


የህብረተሰብ አካላትን የሚያካትት ነው፡፡

የሙያ ማህበራት፡- ሙያቸውን መሠረት አድርገው የተደራጁ ማህበራት


ሲሆኑ፡-
 እንደ ሠራተኞችና መምህራን፣

 የጤና ባለሙያዎችና

 ሌሎች ሙያ ነክ የሆኑ ማህበራትን/አደረጃጀቶችን ያጠቃልላል፡፡


የቀጠለ…

 ሌሎች የሕዝብ ክንፍ አካላት፡-


 በዋናነት የግል ሴክተሩን የሚመለከት ሆኖ ልማታዊ ባለሀብቱ ከመንግስት ክንፉ ጋር በጋራ
የሚጫወተውን ሚና በማጠናከር የድርሻውን የሚወጣ አካል ለማድረግ ነው፡፡
እነዚህ አካላት የግል ሴክተሩን የሚወክሉ አደረጃጀቶችን በመፍጠር፡-
 እንደ ንግድ ምክር ቤት፣
 የንግድ ዘርፍ ምክር ቤት፣
 አሠሪዎች፣ ፌደሬሽን፣ ኮንፌደሬሽንና
 ሌሎች በተመሳሳይ አግባብ ተደራጅተው የሚሰሩትን የሚያጠቃልል ነው፡፡
በተጨማሪም፡-
 የአካል ጉዳተኞች ማህበር፣
 የኃይማኖት ተቋማት የጋራ ምክር ቤት ጉባኤ፣
 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እና ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የህዝብ
ክንፍ አካላት የሚያካትቱ ይሆናል፡፡
ለ. የሕዝብ ክንፍ አጠቃቀምና ሥራ ላይ የሚውልበት አግባብ

 ሁሉም የመንግስት ተቋማት የየራሳቸው ተልዕኮና ዓላማ ላይ የተመሰረተ


አገልግሎት እንዲሰጡ የተቋቋሙ ናቸው፡፡
 በመሆኑም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሕዝብ ውክልና ካላቸው፡-
 የሲቪል ማህበራት፣
 የግል ሴክተርና
 ዜጎች ጋር የሚያገናኝ ሥራ ይኖራቸዋል፡፡
 በዚህ መሠረት ተቋማት በሚሰጡት አገልግሎት ላይ የሕዝብ እርካታን
ለማምጣትና የተገልጋዩን ህብረተሰብ ያሳተፈ አገልግሎት ለመስጠት፡-
 እንደየ ተልዕኳቸውና ልዩ ባሕሪያቸው በተከታታይና በቅርበት ወይም በተዘዋዋሪ
ከተቋማቱ አገልግሎት የሚያገኙ አካላትን ወክለው የተደራጁ የሕዝብ
አደረጃጀቶችን በመለየት፣
 ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በሕዝብ ክንፍነት ማሳተፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. በቀጥታ አገልግሎት ተቀባይ የሕብረተሰብ ክፍል ያላቸው የመንግስት ተቋማት

 እያንዳንዱ ተቋም ከተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚመለከታቸውን የብዙሃን


ማህበራት፣ የሙያ ማህበራት እና የግል ዘርፍ ማህበራት በጥንቃቄ መለየትና ቀጣይነት ባለው
ሁኔታ ማሳተፍ ይጠበቅባቸዋል፣
 የህዝብ ክንፉ በተቻለ መጠን የተደራጀ ተቋማዊ ህልውና ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡
 ይሁንና ወደ ተደራጀ ንቅናቄ ሲገባ የህዝብ አደረጃጀቶች በሚፈለገው ዓይነትና ብዛት ሊሳተፉ
ይገባል፣
 በየተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት በዝርዝር በመለየት የሕዝብ ክንፍ አውቆት መንቀሳቀስ
ይኖርበታል፡፡
 በሂደትም ይህ አካል፡-
 የበለጠ አቅምና ተሰሚነት እንዲኖረው ለማድረግ፣
 ወደ ተደራጀ ኃይል እንዲሸጋገርም ጭምር አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ሁሉ ማድረግ
ይገባል፡፡
2. በተዘዋዋሪ አገልግሎት ተቀባይ የህብረተሰብ ክፍል ያላቸው የመንግስት ተቋማት

 ተቋማት ከተሰጣቸው ተልዕኮና ካላቸው ልዩ ባህርይ አንጻር፡-


 በውስጥ አገልግሎት ላይ የታጠሩ፣
 ከውጭ ተገልጋይ ጋር ፊት ለፊት የሚያገናኝ አሠራር የሌላቸው የፖሊሲና የሌሎች
አስፈጻሚ አካላትን የስራ ክንውኖች የመከታተል፣
 ከተቋማቱ በየጊዜው የሚቀርቡ ሪፖርቶችን የመገምገም፣
 የምርምርና ጥናት ሥራ የመስራት ኃላፊነት የተሰጣቸውን ተቋማት በዋናነት ይመለከታል፡፡

 እነዚህ ተቋማት በቀጥታ አገልግሎት ተቀባይ የሕብረተሰብ ክፍል ሊኖራቸው ስለማይችል


በአብዛኛው የመንግስት ተቋማት የሕዝብ ክንፍ የሆኑትን በመለየት የራሳቸው የሕዝብ ክንፍ
እድርገው በቋሚነት ማሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡
አሰራር
 ከአሰራር አንጻር ሲታይ ከላይ በተመላከተው የህዝብ ክንፍ አደረጃጀት
መሠረት ተቋማት አገልግሎት የሚሰጧቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን
የሚወክሉ የህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶችን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
 ይህም፡-
 በክልል፣ በዞን፣ በልዩ ወረዳ፣ በወረዳና በከተማ አስተዳደር የሚወከሉ የህዝብ ክንፎች
እና
 በቀበሌ አስተዳደር በሚገኙ ተቋማት የሚሣተፉ ዜጎች/ነዋሪዎችን ማለት ነው፡፡

 ከዚህ መነሻ በህዝብ ክንፍ ተሣትፎ ዙሪያ ተቋማት የሚከተሉትን


የአሰራር ስርዓት መከተል አለባቸው፡፡
ከአሰራር አንጻር፡-

 የመንግስት ተቋማት የህዝብ ክንፋቸውን ለይተው ወደ ተግባር ለመግባት እንደየ ተቋማቱ

ባህርይ የሚከተሉትን ሁለት መንገዶች እንደ አማራጭ በመጠቀም ማሳተፍ አለባቸው፡፡


 በሁሉም የአስተዳደር እርከኖች የተደራጁ ማህበራት ሲኖሩ በየአስተዳደር እርከኑ ያለው

ተቋም እንደየ ባህርይው እየለየ ያሣትፋል፡፡


 ለምሳሌ፡- የህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ

 በወረዳ ደረጃ መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማህበራትን፣

 በዞን ደረጃ የህብረት ሥራ ዩኒየኖችን፣

 በክልል ደረጃ የህብረት ሥራ ፌዴሬሽኖችንና ሌሎች ተገቢነት ያላቸውን

አደረጃጀቶችን ያሣትፋል፡፡
የቀጠለ--------------------
 ማህበራት በወረዳና በዞን በሚኖሩበት ጊዜ የክልል ተቋማት የህዝብ ክንፋቸውን

የሚያሣትፉት ከዞን፣ ከልዩ ወረዳና ከተማ አስተዳደር በቂ ናሙና በመውሰድ

ያሣትፋሉ፡፡

 ለምሳሌ፡- የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ

 የትራንስፖርት ማህበራትንና ሌሎች ከሴክተሩ ጋር ተገቢ ግንኙነት ያላቸውን

አደረጃጀቶች ከየተደራጁበት የአስተዳደር እርከን በመውሰድ ያሣትፋል፡፡

 በቀበሌ ደረጃ የሚገኙ ተቋማት በቀጥታ ዜጋውን/ነዋሪውን ማሣተፍ አለባቸው፡፡


የህዝብ ክንፍ ተግባርና ኃላፊነት

 የሚወክሉትን የህብረተሰብ ክፍል መብትና ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት ማሰከበር፣


 በዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ ወቅት ጉልህ ተሳትፎ ማድረግ፣
 በተቋማት ውስጥ የሚገኝ አደረጃጀት አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችሉ ቅድመ-
ሁኔታዎችን ተቋማት ለተገልጋዮች እንዲያሳውቁ ማድረግ፣
 ከህዝብ ክንፉ የሚጠበቁ አስተዋጽኦዎችንና ግዴታዎችን ተገንዝቦ በቁርጠኝነት
መፈጸም፣
 በሚፈጠረው የህዝብ ክንፍ የውይይት መድረክ የተቋሙ የአፈጻጸም ደረጃንና
የለውጥ ስራዎችን አካሄድ በጥልቀት በመገምገም ተገቢውን አስተያየት መስጠት፣
 የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰቦችና ተግባራት
ሲያጋጥሙ ቅድሚያ ራስን ነጻ የማድረግና ሌላውን መታገል፣
የቀጠለ--------------------

 የራስን አቅም ለመገንባት እንዲያስችል፡-


 ከአቅም መገንቢያ የመንግስት ተቋማት፣
 ከግል ድርጅቶች፣
 ከበጎ አድራጊዎችና ሌሎች ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር አቅምን መገንባት፣
 የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ቢያንስ በየወሩ
የሚመለከተውን ተቋም ምልከታ ማድረግ፣
 እያንዳንዱ ተቋም መደበኛ ሪፖርት ለሚመለከተው አካል ከማቅረቡ በፊት በሕዝብ
ክንፍ ማስገምገም አለበት፡፡
 ሌሎችን ተዛማጅነት ያላቸውን ተጨማሪ ተግባራትን ማከናወን ይኖርባቸዋል፡፡
የመንግስት ተቋማት ተግባርና ኃላፊነት
 የህዝብ ክንፉን በአግባቡ በመለየትና የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት፣

 የህዝብ ክንፉን በተቋሙ ተልዕኮ፣ ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ አቅሙን መገንባት፣

 አገልግሎትን በስታንዳርድ ከመስጠት አንጻር የዜጎች ቻርተርን ለህዝብ ክንፉ አቅርቦ በማወያየት የጋራ ስምምነት ላይ

መድረስ፣
 ለህዝብ ክንፉ ወቅታዊ መረጃ በመስጠት በዕቅድ ዝግጅት፣ ትግበራ፣ ግምገማና ምዘና ማሳተፍ፣

 በተቋሙ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና ኪራይ ሰብሳቢነት እንዲከስም መርሀ-ግብር በመንደፍ ከህዝብ ክንፉ ጋር

ተቀናጅቶ ተግባራዊ ማድረግ፣


 በለውጥ ስራዎች ያሉትን የአመለካከት፣ የክህሎትና የግብዓት ችግሮች በመለየት በየሶስት ወሩ በሚኖረው የህዝብ ክንፍ

የውይይት መድረክ ራስን ለአስተያየት ዝግጁ ማድረግ፣


 ስለ ተቋሙ አገልግሎት አሠጣጥና ከህዝብ ክንፉ ስለሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች ቀድሞ ማሳወቅ፣

 በተቋሙ የሚከሰቱ ቅሬታዎችንና ከህዝብ ክንፉ የሚሰጡ አስተያየቶችን ትኩረት ሰጥቶ በማዳመጥ ተገቢ፣ ወቅታዊና

ፍትሃዊ ምላሽ መስጠት፣


 ተቋሙ ለህዝቡ በዜጐች ቻርተር ስታንዳርድ መሠረት አገልግሉት እየሰጠ መሆኑን ማረጋገጥ፣

 ሌሎች ተዛማጅነት ያላቸውን ተጨማሪ ተግባራትን ማከናወን ይኖርባቸዋል፡፡


የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሴክተር ተግባርና ኃላፊነት

 የህዝብ ክንፉ ሚናውን የሚወጣበትንና የሚመራበትን የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት፣


 በአሰራር ሥርዓቱ ዙሪያ ለህዝብ ክንፉና ለመንግስት ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ
ሥልጠና መስጠት፣
 ስለ አሰራር ስርዓቱ ተግባራዊነት ክትትልና ግምገማ ማድረግ፣
 የህዝብ ክንፉ መብትና ግዴታውን እንዲያውቅ ግንዛቤ መፍጠር፣
 የህዝብ ክንፉ ተቋማትን በፍትሀዊነትና በግልጽነት መገምገምና መመዘን የሚችልበትን
አቅም ማሳደግ፣
 የህዝብ ክንፉ የተመሠረተበትን ዓላማ መሠረት ያደረገ የጠያቂነት አቅም ማሳደግ፣
 የህዝብ ክንፉ ተቋማትን በሚመዝኑበት ወቅት የማስተባበርና ጥሬ መረጃውን
በመውሰድ ተንትኖ ውጤቱን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ፣
 ሌሎች ተዛማጅነት ያላቸውን ተጨማሪ ተግባራትን ማከናወን፣
የህዝብ ክንፍ ናሙና ቢጋርን በሚመለከት
 ሴቶች ማህበር
 ወጣቶች ማህበር
 መምህራን ማህበር
 ንግድ ምክር ቤት
 የንግድ ዘርፍ ምክር ቤት
 የአካል ጉዳተኞች ማህበር
 የኃይማኖት ተቋማት የጋራ ምክር ቤት ጉባኤ
 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
 መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማህበራትን
 የህብረት ሥራ ዩኒየኖችን
 የህብረት ሥራ ፌዴሬሽኖችን
 የትራንስፖርት ማህበራትን፣ የግንባታ ተቋራጮች ማህበራትን፣
 የግል ተሸከርካሪ ማሰልጠኛ ማህበራት
(40% )የህዝብ ክንፉ ተቋማትን የሚመዝንበት ዋናና ዝርዝር መስፈርቶች

ተ.ቁ ዋናና ዝርዝር መስፈርቶች ክብደት

1 አሳታፊነት 10
2 ግልጸኝነት 15
3 ቶሎ ምላሽ ሰጭነት 25
4 ተጠያቂነት 15
5 አቅም መገንባት 10
6 የዕቅድ አፈጻጸም ውጤታማነት 10
100
ህዝብ ክንፍ ተቋማትን የሚመዚንበት አግባብን በሚመለከት

 የተቋሙ ህዝብ ክንፍ ቁጥር ከአንድ በላይ ከሆነ የሁሉም ህዝብ ክንፍ ተወካዮች
በመገኘት ተቋሙን እንዲመዝኑ ተደርጎ አማካይ ውጤቱ ይወሰዳል፡፡
 ተቋሙን መመዘን የሚችለው የህዝብ ክንፍ ተወካይ በበጀት ዓመቱ የተቋሙ

ሥራዎች ውስጥ ተሳትፎ ያደረገና መረጃ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡


 ህዝብ ክንፍ ተቋማትን ከ40% ይመዝናሉ
 የተቋማት አፈጻጸም ከ60 % ይመዘናል፡፡
 በአፈጻጸም ደረጃ ተቋማትን በሚመለከት፡-
 በጣም ከፍተኛ-------------- -----------5 ( 95-100 )
 ከፍተኛ አፈጻጸም---------- -------------4 ( 80-94 )

 አጥጋቢ አፈጻጸም----------------------- 3 ( 65-79 )

 ዝቅተኛ----------------------------- 2 ( 56-60 )

 በጣም ዝቅተኛ-------------- -----------1 ( ከ55 በታች


የመልካም አስተዳደር መርሆዎችና የትግበራ ማኑዋል

 መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፡-


 የመልካም አስተዳደር ችግሮች ልየታና መፍቻ እቅድ በማዘጋጀት ትግበራውን
በጠንካራ ክትትልና ድጋፍ አሰራር አስደግፎ መረባረብን ይጠይቃል፡፡
 እስካሁን ባለው ሁኔታ፡-
 የልየታ ጥራት ችግር፣ የግንዛቤ፣ የዕውቀት እና የክህሎት ማሳደጊያ ስራችን
በየደረጃው በተደራጀና ወጥነት ባለው በትግበራ ማኑዋል መነሻ እየተመራ
አይደለም፡፡ ከዚህም የተነሳ ከመዋቅር መዋቅር ጉራማይሌ አፈጻጸም እየታየ
ይገኛል፡፡
 በመሆኑም፡- በዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ ዙሪያ የሚታዩ የዕውቀትና
የክህሎት ክፍተቶችን በመሙላትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ
አፈጻጸምን ውጤታማ ማድረግ እንዲሁም የዜጎች እርካታ ለማረጋገጥ
እንዲቻል ይህ የመልካም አስተዳደር የትግበራ ማኑዋል ላይ
መመካከር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝተዋል፡፡
የመልካም አስተዳደር መርሆዎች
 የተለያዩ ፀሐፊዎች በቁጥራቸውና በአከፋፈላቸው የተለያዩ የመልካም
አስተዳደር መርሆዎችን ያስቀምጣሉ፡፡ ከአገራችን ተጨባጭ 8ቱ የመልካም
አስተዳደር መርሆች፡-
 የህግ የበላይነት
 ተጠያቂነት
 ተሳትፎአዊነት
 ግልፅነት
 ቶሎ ምላሽ መስጠት
 የጋራ መግባባት
 ቀልጣፋና ውጤታማነት
 ፍትሃዊነት
1. የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣
 መንግሥት ህዝብ በተስማማባቸው ህጐች አጥር ውስጥ ታጥሮ እንዲሰራ
ያደርጋል፣
 የህግ የበላይነት ጉልበተኛውም ደከም ያለውም መብትና ጥቅሙን

የማስጠበቅ እድል እንዲያገኘ የሚያደርግ መሳሪያ ነው፡፡


 ዘላቂ ሰላም ሊኖር የሚችለው ህጐች ልዕልና ሲኖር ነው

2. የጋራ መግባባት (Consensus Oriented)


 የጋራ መግባባት በራእይ ላይ፣ በግብ ላይ፣ በመርህ ላይ የጋራ አመለካከት

መያዝ ነው፣
 ለጋራ ጉዞ የጋራ መነሻ የሚሰጥ ነው፡፡
 የጋራ መግባባት ሲኖር ፈተናዎችን ሁሉ አንድ ላይ ቆሞ በቆራጥነት

የመወጣትና ለስኬት መብቃት ይቻላል፤


 መግባባት ሲኖር በጋራ ችግሮች ላይ የጋራ መፍትሔ ማበጀት ይቻላል፣
3. ግልጽነት(Transparency)

 ግልጽነት ዜጎች በቂ መረጃ ያላቸው ሆነው ተገቢውን አቋም እንዲይዙ


ያስችላል፡፡
 ግልጽነት አሳታፊነትን ያጠናክራል፣

 ህዝቡ የመንግስት አገልግሎትን የልማት ስራዎችን በተመለከተ መረጃ

የማግኘት መብቱን ከተነፈገ ለመንግስት ያለው እምነቱ ይሸረሸራል፡፡


 ይህ ደግሞ የህዝብ ቅሬታን ይፈጥራል፡፡

4.ተጠያቂነትን ማስፈን (Accountability)


 የመንግስት አካላት(አመራር፣ ፈጻሚ) ለሚሰሩት ስራ ሀላፊነትና ተጠያቂነት

እንዲኖራቸው ማድረግ ጥሩ የሰሩትን ማበረታታት እና ባጠፋው ላይ ህጋዊ


የማስተካከያ እርምጃ መውሰድን ያጠቃልላል፣
 ተጠያቂነት የሌለበት አሠራር በሰፈነበት ሁኔታ ስለመልካም አስተዳደር፣

ስለዴሞክራሲ፣ ስለ ሕዝብና ዜጎች መብት መናገር ስማዊ መሆኑ ብቻ ሳይሆን


ሕዝብ አመኔታ ያጣል፣ ሥርዓቱንም አደጋ ላይ ይጥላል፡፡
5. አሳታፊነት(participatory)real engagement.docx
 በዕቅድ ዝግጅት፣ አተገባበርና አፈፃፀም ላይ ማሳተፍና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ፣
 ከዜጎችና ከተገልጋዮች ጋር ቋሚ፣ ቀጣይነት ያለውና በዕቅድ ላይ የተመሠረተ ውይይት

ማድረግና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ፣


 ከፈፃሚው ጋር ቋሚና በዕቅድ ላይ የተመሠረተ ውይይት ማድረግ እና
 ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍና አብሮ መስራት፣

6. ፍትሐዊነትና አካታችነት
 ፍትሀዊነትና አካታችነት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ጠቃሚ ከሆኑ መርሆዎች አንዱ ነው፣
 ሁሉም ዜጎች በተለይም ደግሞ ቀደም ሲል የተገፉና የልማቱ ተጠቃሚ ያልሆኑ የህብረተሰብ

ክፍሎች በፍትሀዊነት የሚጠቀሙበትንና ኑሮአቸውን የሚያሻሽሉበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠርን


ያመለክታል፡፡
 በዕቅድ ዝግጅት፣ በአፈጻጸምና በሪፖርትም ጭምር

 የሴቶችን፣
 የአካል ጉዳተኞችን፣
 የአነስተኛ ተዋጽኦ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን፣…ወዘተ
ጉዳዮችን ያገናዘበና መብቶችና ጥቅሞቻቸውን ያስጠበቀ ማድረግ ፣
የቀጠለ---------------------------
 የሚወጡ ሕጎች፣ በተግባር ላይ የሚውሉ የአሠራር ሥርዓቶች ከአድሎ የፀዱና
ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ
አለባቸው፡፡
 7. ቶሎ ምላሽ መስጠት (Responsiveness)
 ከተገልጋይ/ከሕዝብ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች እንደየጥያቄዎቹ ቅደም ተከተል

ፈጥኖ ምላሽ መስጠት፣


 ጥያቄው ተገቢም ይሁን አይሁን በተቀመጠው የህግ አግባብ መሠረት

የሚገባውን ምላሽ በወቅቱ መስጠት፤


 ስለተሰጠውም ምላሽ በአጥጋቢ ሁኔታ ማስረዳት ይጠበቃል፡፡
 አገልግሎት ጠያቂ ሕዝብ በሰበብ አስባቡና የእርሱ ጉዳይ ባልሆኑ የአሠራርና

የሥነ-ምግባር ችግሮች በየአገልግሎት መስጫ ተቋማት ሊመላለስና ደጅ


ሊጠና አይገባውም፡፡
8. ውጤታማነትና ቅልጥፍና

አንድን ተጨባጭ ስራ በአነስተኛ ወጪ ፣ ጊዜ …ወዘተ ለመስራት


የመቻል ጉዳይ ነው፡፡
 ውጤታማነት አንድን ሥራ የተቀመጠለትን ግብና ዓላማ ለማሳካት
በሚያስችል አኳኋን መፈፀም ነው፡፡
አንድን ሥራ ስራው የሚጠይቀውን አነስተኛ ጊዜና ገንዘብ ወጪ
በማድረግ መስራት ትርጉም የሚኖረው የተሰራው ሥራ
የተቀመጠለትን አላማና ግብ ማሳካት ሲችል ብቻ ነው፡፡
አላማና ግብን ያላሳካ ሥራ በቅልጥፍናም ቢሰራ በቅልጥፍና የተሰራ

ኪሳራ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም፡፡


መልካም አስተዳደርን የማስፈን ጠቀሜታ፡-
 የመልካም አስተዳደር መረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የተለያዩ
ጥናታዊ ፅሑፎች ይገልጻሉ፡፡ የመልካም አስተዳደር መስፈን፡-
 የዜጎችን እምነትን /TRUST/ ይጨምራል
 አዎንታዊ አመለካከትን ያዳብራል
 ወጪን ይቀንሳል/LOWERS THE COST OF CAPITAL/
 ብክነትን፣ ስጋትን፣ ሙስናንና የተሳሳተ አመራርን ይቀንሳል
 5.ፍትሀዊ አሰራርን ያሰፍናል
 ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት ቀጣይነትን ያረጋግጣል
መልካም ያልሆነ አስተዳደር ምንነትና መገለጫ ባህሪያት
 መልካም ያልሆነ አስተዳደር የመልካም አስተዳደር ተቀራኒውን ገጽታ የያዘ
ሲሆን ፡-
 ሙስናና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን፣
 የግልጽነትና የተጠያቂነት አሰራር መጓደልን፣
 ፈጣን ምላሽ አለመስጠትን፣
 የመንግስትንና የህዝብን ሀብት በቁጠባና በውጤታማነት ስራ ላይ ማዋል አለመቻልን
እና የህግ የበላይነት አሰራር አለመስፈንን የሚያጠቃልል ነው (ዋኤል ኦምራን፡2013)፡፡
 መልካም ያልሆነ አስተዳደር በአንድ አገር ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ለሚታዩ ሌብነትና
ብልሹ አሰራሮች እንደ ዋነኛ መንስኤ እንደሆነ ብዙ ጥናታዊ ፅሁፎች ይገልጻሉ፡፡
የመልካም አስተዳደር ችግር የሚያስከትለው አደጋ
 የሌብነትና ብልሹ አሰራር ያሰፍናል፡-
 ህዝብ በመንግስት ላይ ያለውን እምነት ይሸረሽራል፣
 ሥርዓት አልበኝነት በእጅጉ ያበረታታል፤

አስተዳደርን በማስፈን ሂደት የተለያዩ አካላት ሚና


1. የህዝብ ተወካዮች ሚና
 መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ህጎችን በማውጣት፤
 የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን የመልካም አስተዳደር አፈጻጸም በመከታተልና

ቁጥጥር በማድረግ፤
 ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፤
የቀጠለ-------------------------
2. የአመራሩ ሚና

 በመንግስታዊ አካሉ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች ተግባራዊነት ወይም አፈፃፀም የሚመዘንበት

ስርዓት መዘርጋት፤
 በመ/ቤቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ትንተና ላይ የተመሠረተ የመ/ቤቱ የመልካም አስተዳደር

ዕቅድ እንዲታቀድ ማድረግ፤


 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ በፈፃሚውና በህዝብ ክንፉ ተሳትፎ

እንዲፈፀም ማድረግ፤
 ከፈፃሚውና ከህዝብ ክንፉ ጋር በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ቋሚ ውይይት ማድረግ፤
 የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት፣
 በየጊዜው በመገምገም ለችግሮች መፍትሄ በማስቀመጥ፣
 ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ስልቶችን በመቀየስ አጠቃላይ ዕቅዱን በባለቤትነት መምራት፣
የቀጠለ-----------------------------
4. የፐብሊክ ሰርቪሱ ሚና፡-
 ፐብሊክ ሰርቪሱ የመንግሥትን አገልግሎት ለሕዝብና ለዜጋው ለማድረስ

የተደራጀ የመንግሥት የማስፈጸሚያ ዋነኛው መሣሪያ ነው፡፡


 በመሆኑም ፐብሊክ ሰርቪሱ፡-

ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ራሱን ነጻ


በማድረግ ሎሎችም ነጻ እንዲሆኑ መታገል ይጠበቅበታል፣
የውስጥና የውጭ መልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት
የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ትግበራ፣ አፈፃፀሙን
በመከታተልና፣ በመገምገም እንዲሁም ግብዓት በመስጠት
በግንባር ቀደምነት መሳተፍ፣
የቀጠለ-------------------------
5.የህዝብ ክንፍ ድርሻ

 ህዝቡ ጥቅሙን የሚጎዳ፣ የኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና አስተሳሰብና ድርጊት


እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመታገል፣
 በመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ውስጥ የመንግስት አጋር በመሆን በቂ ተሳትፎ
በማድረግ፣
 መብቱን በህጋዊ መንገድ ማስከበርና ለመብቱ መቆም፣
 የመንግስት ሀላፊዎችና ሰራተኞች ለሚሰጡት ፍትሀዊ ያልሆነ አገልግሎት
ተጠያቂ ማድረግ፣
 ነጋዴ ህብረተሰቡና ማህበራት የንግድ ስርዓቱን የሚያደናቅፉ ተግባራትን
ማጋለጥ፣ ህገ-ወጦችን ከመንግስት ጎን በመቆም መቆጣጠር፣
 ቀልጣፋና የተሻሉ አሰራሮች የሚፈጠሩበትን መንገድ መጠቆም፣
 የአሰራር ክፍተቶች በሚታዩበት አካባቢ ግብአት መስጠት፣
የቀጠለ-----------------------
6. የመገናኛ ብዙኃን/ሚዲያ ሚና፡-
 የመልካም አስተዳደር መርሆዎች ከሚዲያ ጋር ቀጥታ የሆነ ግንኙነት አላቸው፡፡
ስለዚህ፡-
 ለዜጎች የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን ማስተዋወቅ፣
 የህዝብ ተሳትፎ ቀጣይነት እንዲኖረውና እንዲጎለብትና ማድረግ፣
 ለህዝቡ ወቅታዊ መረጃ በመስጠት በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ትግል እንዲያደርግ ማነሳሳት፣
 በአርአያነት የሚጠቀሱ ስራዎች እንዲሰፉና ኢፍትሀዊ የሆኑ አሰራሮች እንዲስተካከሉ ማድረግ፣
 የመልካም አስተዳደር ስርዓት የሚያደናቅፉ ተግባራትን ማጋለጥ፣ ህገ-ወጦችን ከመንግስት ጎን
በመቆም መቆጣጠር
 የተጠያቂነት አሰራር እንዲሰፍን ማድረግ፣
 በመንግስት አገልግሎቶች ቀልጣፋና የተሻሉ አሰራሮችን የሚፈጠሩበት መንገድ መጠቆም፣
 የአሰራር ክፍተቶች በሚታዩበት አካባቢ ግብአት በመስጠት አገራዊ ድርሻ መወጣት ፡፡
የዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ

 ዕቅድ ምንነት፡-
 ዕቅድ የስራ አመራር ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡
 ዕቅድ ነገን ለመያዝ የሚጠመድ ወጥመድ ነው (Allen)
 ዕቅድ ከአማራጭ ዓላማዎች፣ ግቦች፣ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎች፣ ፕሮጀክቶች

እና ፕሮግራሞች የተሻለውን መምረጥንም ያካትታል (Billy E. Goetz) ፡፡


 ዕቅድ ማለት ምን እንደሚደረግ? ለምን እንደሚደረግ? እንዴት

እንደሚደረግ? በማን እንደሚደረግ? የት እንደሚደረግ? መቼ


እንደሚደረግ? አስቀድሞ የመወሰን ሳይንስና ጥበብ ነው (Theo
Haimann)፡፡
 በመጨው ዘመን ምን ምን መሰራት እንዳላበት፣ እንዴት፣ መቼ እና በማን

እንደሚሰሩ የመወሰን ሂደት ነው፡፡


የመልካም አስተዳደር ችግሮች ምንነትና ልየታ
 የመልካም አስተዳደር ችግር ምንነት፡-
 የሁሉም ወይም ከፊል የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በአግባቡ ካለመተግበር

ወይም በአተገባበር ጉድለት ምክንያት የሚመነጩ አስተዳደራዊ ችግሮች


(Governance deficit which is more of systemic) ናቸው፡፡
 እነዚህ ችግሮች የሚፈቱትም መርሆዎችን በአግባቡ በመተግበር ነው፡፡
 ችግሮቹ ከውጭና ከውስጥ ተገልጋዮች ፍላጎት ጋራ የተቆራኙ ናቸው፡፡

 የመልካም አስተዳደር ችግሮች መለያ ስልቶች፡-


 ከዜጎች፣ ከህዝብ ክንፍ እና ከባለድርሻ አካላት ከሚቀርቡ ቅሬታዎችና
ጥቆማዎች (በመድረኮች፣ አስተያየት ማሰባሰቢያ መዝገብና የሃሰብ መስጫ
ሳጥኖች፣ በአካል ከሚቀርቡ መረጃዎች)፣
 በዕቅድ አፈጻጸም ክትትልና ድጋፍ (ሪፖርት፣ ሱፐርቪዥን፣ግምገማ)፣
 በዳሰሳ ጥናቶች፣
 ከህትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ፣
የመልካም አስተዳደር ችግሮች ምንነትና ልየታ…

በመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍቻ ዕቅድ ዝግጅት ሂደት የትኩረት ነጥቦች፡-


 ከመርሆዎች አተገባበር አንጻር የነባራዊ ሁኔታ ትንተና በማካሄድ ችግሮችን
መለየት፣
 የተለዩ ችግሮችን እንደወረዱ ማስቀመጥ፣
 ችግሮችን እንደየክብደታቸው (እርካታ የመፍጠር ተጽእኖ ገዥነት፣
አንገብጋቢነት፣ የሚያስከትለው አደጋ፣ የተጣሱ መርሆዎች ብዛት፣ ወዘተ)
በቅደም ተከተል ማስቀመጥ፣
 ችግሮችን ከመልካም አስተዳደር መርሆዎች አንጻር ለይቶ መፈረጅ ፣
የችግሮችን መንስኤ መለየት፣

ተመሳሳይ መንስኤ ያላቸውን ችግሮችን በየፈርጃቸው ማደራጀት፣

ተመሳሳይ መንስኤ ያላቸው ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ግቦችን

መቅረጽ፣
እያንዳንዱን ግብ ለማሳካት የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን መለየት፣

ጊዜ (በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም)፤ ፈጻሚ አካል እና የሚጠበቅ ውጤት፣


የችግሮች በቅደም ተከተል መለያ ዋና ዋና መስፈረቶች፡-

1. እርካታ የመፍጠር ተጽዕኖ


 ችግሩ በመረታዊ ባህሪያቸው ከአገልግሎት ተጠቃሚ ዜጋ ጋር ያለው ቀጥተኛ

ትስስር፣
 ችግሩን መፍታት የዜጎችን እርካታ ከማሳደግ አንጻር የሚኖረው ድርሻ እና
 ችግሩ አብዛኞቹ በመርሆች መጣስ ምክንያት የተፈጠረ ስለመሆኑን በጥልቀት

በመፈተሽ ይሆናል፡፡
2. ገዥነት
 ችግሩ በመሰረታዊ ባህሪው ቁልፍ የሆነ፣
 ከብዙ ጉዳዮች ጋር የተያዘ፣
 ችግሩን በመፍታት ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ችግሮች ለመፍታት

የሚያስችል እና
 በበርካታ መርሆች መጣስ ምክንያት የተፈጠረ ከሆነ በመፈተሽ ይሆናል፡፡
የቀጠለ------------------------------------

3. አንገብጋቢ፡-
 ችግሩ ፈጣን ምላሽ የሚሻ፣
 በወቅቱ ካልተፈታ ለተጨማሪ ወጪ የሚዳርግ እና
 የችግሩ መፈታት ለሌሎች ችግሮች መፈታት በቅድመ ሁኔታነት የሚታይ

መሆኑን በመሰሰፈተሽ ይሆናል


4. የሚያስከትለው አደጋ፡-
 ችግሩ ካልተፈታ በአገልግሎት ሰጪ ተቋምና በመንግስት ላይ በቀጣይ
በሚኖራቸው አመኔታ ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተፅዕኖ እና
 ይህ ሁኔታም በአገልግሎት ሰጪው ተቋም ህልውና እንዲሁም በአገር ደረጃ

የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ አንዴምታ በመፈተሽ


ይሆናል፡፡፡፡
ምሳሌ 2.፡- የመልካም አስተዳደር ችግሮች ቅደም ተከተል ማሳያ
ተ.ቁ የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እርካታ አንገብጋቢነ የሚያስከትለ ደረጃ
ገዥነት ድምር
የመፍጠር ተጽእኖ ት ው አደጋ

የተሰጠው የተሰጠው የተሰጠው


የተሰጠው ክብደት ድምር
ክብደት ክብደት ክብደት(በ5% (ከ20%)
(በ5%)
(በ5%) (በ5%) )
1 ለሚቀርቡ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች
ቅድመ-ሁኔታዎችን በግልጽ 4 4 5 3 16 5
አለማሳወቅ፣
2 ከተጠያቂነት ስርአት መላላት ጋር
5 4 5 5 19 2
ተያይዞ የሚፈጠር ሥርዓት አልበኝነት፣
3 ቀልጠፋ፣ ውጤታማና ፍትሐዊ
5 5 5 5 20 1
አገልግሎት መስጠት አለመቻል፣
4 በሰው ኃይል፣ በአሰራር፣ በአደረጃጀት
እና በአመለካከት ክፍተት ምክንያት 4 5 4 4 17 4
የሚፈጠሩ የአገልግሎት መጓደሎች፣
5 የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ከኪራይ
ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የፀዳ 5 4 4 5 18 3
አለመሆን፣
የእቅድ ዝግጅት እና ትግበራ አቅጣጫዎች

 የእቅድ ዝግጅት አቅጣጫዎች፡-


 የተቋሙን ተጨባጭ ሁኔታ ለእቅድ ዝግጅት መነሻ በማድረግ በጥልቀት
መዳሰስ፣
 አገራዊ የመንግስት አቅጣጫንና የመልካም አስተዳደር ፓኬጅ (ዕቅድ) እንደ
መነሻ መውሰድ፣
 የመልካም አስተዳደር ችግሮች የአፈታት ስልቶችን በግልፅ በእቅድ
ማስቀመጥ፣
የቀጠለ------------------------------------

 የእቅድ ትግበራ አቅጣጫዎች፡-


 በለውጥ ቲም አግባብ መፈጸም፣
 የለውጥ መሣሪያዎችን አቀናጅቶ መጠቀም
 ፈጣን ለውጥ አምጭ /Quick Wins/ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ፣
 በዜጎች የነቃ ተሳትፎ መፈጸም፣
 የዜጎችና ተገልጋዮች እርካታን እየለኩ እና ውጤቱን በግብአትነት እየጠቀሙ
መፈጸም፣
 ምርጥ ተሞክሮን መለየት፣መቀመርና ማስፋት
 ተጠያቂነትን እያረጋገጡ መተግበር
ስለሰጣችሁኝ ጊዜ
አመሰግናለሁ!

You might also like