Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 60

አደጋ መከላከልና መቆጣጠር

ስልጠና ኢንስቲትዩት

ግንቦት 2010 ዓ/ም


አዲስ አበባ
የአደጋ መቆጣጠር
ዕዝ
ስርዓት(አመዕስ)
ዓላማዎች

ሰልጣኞች ይህን ስልጠና ካጠናቀቁ በኋላ፡-


የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት ምንነትን ይረዳሉ

 የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት አስፈላጊነት ይገነዘባሉ

የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓትን ተቋማዊ አደረጃጀት ያብራራሉ

የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓትን ገጽታዎችን ያብራራሉ


1. የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት (ICS)
አመሰራረት፤ ትርጉምና አላማ
1.1 አደጋ ማለት ምን ማለት ነው?

አደጋ ማለት በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ ምክንያት


ሊከሰት የሚችል ሲሆን በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ
የከፋ ጉዳት ሳያስከትል አፋጣኝ ምላሽ የሚያስፈልገው
ክስተት ነው፡፡
ወይም በተፈጥሮም ሆነ በሰዉ ሰራሽ አማካኝነት በሚከሰቱ አደጋዎች
/hazards/ የሚደርስ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት
(እልቂት) ማለት ነው፡፡
መገለጫዎች፡-

 የበርካታ ሰዎች ህይወት ህልፈት፣

 አካላዊና አዕምሮአዊ ጉዳት፣

በንብረት ላይ የሚደረስ ከፍተኛ ውድመት እንዲሁም በአካባቢ ላይ


የሚደርስ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል
በአጠቃላይ
ማህበራዊ፣

ኢኮኖሚያዊና

ፖለቲካዊ ቀውስ

መጥፎ ትዉስታን ጥሎ የሚያልፍና

 ጭንቀትን የሚፈጥር ክስተት ነው፡፡


የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት (ICS) ማለት ምን ማለት
ነው?
የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት ማለት በማንኛውም
የአደጋ/ክስተት ዓይነት ወይም ስፋት ወይም መጠን ምላሽ
ለመስጫነት ቢተገበር ውጤት ሊያስገኝ የሚያስችል የሥራ
አመራር ስርዓት ነው፡፡
አመዕስ ወጥነት ያለው አሰራር የሚፈጥር፣ እንዲሁም

ውጤታማና ቀልጣፋ የአደጋ ዝግጁነት፣ ምላሽ አሰጣጥ እና


ጊዜያዊ ድጋፍ/መልሶ እስከ ማቋቋም ድረስ ያለውን የአደጋ ስራ
የአሰራር ስርዓት የሚያጠናክር የአደጋ ስራ አመራር መሳሪያ
ነው፡፡
የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት ወጥ የሆነ (standardized)፣
በአደጋ ቦታ የሚተገበር(on scene)፣ ለሁሉም አደጋ የሚሆን
ከማንኛውም ተቋማዊ አደረጃጃት ጋር ሊጣጣም የሚችል
የአደጋ ስራ አመራር ፅንሰ ሃሳብ ነው፡፡
1.2. የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት አመሰራረት

የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት የተመሰረተው የአሜሪካ ክፍለ

ግዛት በሆነችው ካሊፎረኒያ ሲሆን የተመሰረተበት ምክንያትም

በወቅቱ ከባድ የሆነ የሰደድ እሳት ቃጠሎ አደጋ ካጋጠማቸው

በኋላ ነበር፡፡
የሰደድ እሳት ቃጠሎ አደጋ ለ13 ተከታታይ የቆየ ሲሆን

1. 16 ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል

2. ከ700 በላይ የሚደርሱ ተቋማትን አውደሟል


3.ከ500000 በላይ አክሬስ የሚሸፍን ቦታ ተቃጥሏ ል

4.ከ$234 ሚሊዮን ዶላር በላይ አውደሟል


አመዕስ በNFPA የተካተተው በ1970ዎቹ ሲሆን በአሁኑ

ሰዓት ከባድና ወስብስብ አደጋዎችን ለመምራት ሲባል

NFPA1600 ተብሎ በቴክኒክ ኮሚቴው እንዲካተት

ተደርጓ ል
በአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት ምላሽ ያገኙ ነገር ግን በአደጋ ስራ
አመራርና ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ ይታዩ የነበሩ ጉዳዮች፡-
የተጠያቂነት ውስንነት፣

ግልፅነት የጎደለው የመሪና የተመሪዎች ጥምረትን፣

ደካማ የተግባቦት ስርዓት;

 የቃላት አጠቃቀም ችግርን፣


ስርዓትን የተከተለ የዕቅድ ሂደት ውስንነትን፣

አስቀድሞ የተዘጋጀ፣ የተለመደ፣ ቀላልና ተለጣጭ የአደጋ

ስራ አመራር መዋቅር አለመኖርን፣


አስቀድሞ የተለየ በአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት ውስጥ

የሚያሳተፉ ተቋማትን በተዘጋጀው መዋቅር እና በማቀድ


ሂደት ውስጥ የሚያቀናጅ/የሚያጣምር ስልት
አለመኖርን፣ / MACS/
•የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት ለማንኛውም ዓይነት አደጋ
ምላሽ ለመስጠት የተቀረፀ ሲሆን የተለያዩ ተቋማት የአደጋ
ሠራተኞች በፍጥነት ወደ ጋራ የአሰራር መዋቅሩ በማጣመር
ለኦፕሬሽን ስራ የሚያስፈልጉ ግብዓት እና አስተዳደራዊ
ጉዳዮችን በማቅረብ የወጪ መደበላለቅንና መደራረብን
በማስቀረት ወጪ ቆጣቢ የሆነ ስርዓት ነው፡፡
1.3 መሰረታዊ መርሆች
1. በአደጋ ስራ ለሚሳተፉ ባለድርሻ እና አጋር አካላት በጋራ

ሊያግባቡ የሚችሉ ሙያዊ ቃላትን መጠቀም

2. አደጋ ለመቆጣጠር እንደንአደጋው ነባራዊ ሁኔታ ሊለጠጥ ወይም

ሊያንስ የሚችል መዋቅር

3. የተቀናጀ ተግባቦት መኖር

4. ወጥነት ያለው የትዕዛዝ ሰንሰለት


5.ወጥነት ያለው የትዕዛዝ ሰንሰለት መዋቅር

6.የተቀናጀ የአደጋ ስራ ዕቅድ

7.የተጠናከረ የቁጥጥር ስርዓት

8. የተሟላ የአደጋ መቆጣጠር ፋሊቲ

9.ቀልጣፋና ዉጤታማ የሀብት አጠቃቀም


1.4 የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት(አመዕስ) አስፈላጊነት

የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት የሥራ አመራር መርሆዎችን በመተግበር፣ በአደጋ


ስራ ላይ የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፡
የአደጋ ሠራተኞችንና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ፣

ማንኛውም የአደጋ ኦፕሬሽን በእቅድ እንዲመራ ምቹ ሁኔታዎችን

ይፈጥራል፣

ግብዓቶች በአግባቡና በቅልጥፍና ጥቅም ላይ እንዲውሉ

ያስችላል፣
2. የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት(አመዕስ) ገፅታዎች
አመዕስ የተለያዩ ገፅታዎች ያሉት ሲሆን የሚከተሉትን
እንደ አብነት ማየት ይቻላል፡፡
የአመዕስ ተቋማዊ አደረጃጃት
የአደጋ ጊዜ/ኦፕሬሽናል ዕቅድ
የመሪና ተመሪዎች ጥምረት (span of control)
የአደጋ ኦፕሬሽን ፋሲሊቲዎች
ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
የአመዕስ ተቋማዊ
አደረጃጃት

የአደጋ
ጊዜ/ኦፕሬሽናል የቁጥጥር
ዕቅድ ስብጥር
አመዕስ
የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት ገፅታዎች
የአደጋ መቆጣጠር የአመዕስ የሥራ
ፋሲሊቲዎች መደብ፣ ሚና እና
ኃላፊነት
2.1 የአመዕስ ተቋማዊ አደረጃጃት

የአደጋ መቆጣጠር
አዛዥ

የኦፕሬሽን የግብዓት የፋይናንስና


የሥራ የዕቅድ
የሥራ ዘርፍ አቅርቦት አስተዳደር
ዘርፍ ዘርፍ የሥራ ዘርፍ
የአመዕስ አደረጃጃት አካላት
የሥራ ዘርፍ(ሴክሽን)፡- የኦፕሬሽን፣ የዕቅድ፣ የግብዓት፣
እና የፋይናንስና አስተዳደር የሥራ ዘርፎችን የሚይዝ
ሲሆን በዘርፍ ቺፍ የሚመራ ነው፡፡
የስራ ክፍል(ዲቪዥን)፡- የመሬት አቀማመጥን መሰረት
በማድረግ የሥራ ክፍፍል የሚደረግበት ሆኖ በተቆጣጠሪ
(ሱፐርቫይዘር) ደረጃ የሚመራ ነው፡፡
ቡድን፡- ስራን መሰረት በማድረግ የሚደራጅ ሲሆን
በቡድን መሪ የሚመራ ነው፡፡
ግብረ ሀይል፡- የተለያዩ ግብዓቶች (ባለሙያ፣ መሳሪያ፣

ማሽን)) በአንድ መሪ ተጠሪ ሆነው ሲደራጁ ነው፡፡


ስትራክ ቲም፡- አንድ ዓይነት ግብዓቶች በአንድ መሪ

ተጠሪ ሆነው ሲደራጁ ይሆናል፡፡


2.2 የአመዕስ የቁጥጥር ስብጥር
• የቁጥጥር ስብጥር ማለት አንድ ባለሙያ/ፈፃሚ/መሳሪያ
ለአንድ ተቆጣጠሪ ተጠሪ ሆኖ ሪፖርት እና የሥራ ትዕዛዝን
በሚመለከት ከአንድ መሪ ጋር ብቻ የሚደርገው የስራ
ግንኙነት ነው፡፡
• ምን ያህል ፈፃሚዎች ለአንድ ተቆጣጠሪ ተጠርንፈው
ውጤታማ እንደሚሆኑ የሚያሳይ ነው፡፡
• በአደጋ ስራ ላይ መሪ እና ተመሪዎች የቅርብ ግንኙነት
ሊኖራቸው ይገባል፡፡
• አንድ መሪ ቢያንስ 3፣ ቢበዛ 7 በአማካይ 5 ፈፃሚዎችን
ወይም መሳሪያዎችን በትክክልና ውጤታማ በሆነ መልኩ
መምራት እንደሚችል የተለያዩ ጥናቶች ያስቀምጣሉ፡፡
ተቆጣጣሪ

ግብዓት/ ግብዓት/ ግብዓት/


ሀብት 1 ሀብት 2 ሀብት 3
አንድ ለሶስት የቁ

አንድ ለሶስት ስብጥር


• የቁጥጥር ስብጥርን ማስጠበቅ መሪው በስሩ
የሚገኙትን ሀብቶች/ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ፣
በቅልጥፍናና በውጤታማ ሊመራና ስራውን
ሊያስራ የሚያስችል ስርዓት መፍጠር ማለት ነው፡፡
ተቆጣጠሪ

ግብዓት/ሀብት ግብዓት/ሀብት 3
ግብዓት/ ሀብት 2
1

ግብዓት/ሀብት 4 ግብዓት/ሀብት 5

አንድ ለአምስት የቁጥጥር ስብጥር


2.3 የአመዕስ የሥራ መደብ፣ ሚና እና ኃላፊነት
• በአመዕስ አደረጃጃት በአምስቱም የአደጋ ስራ
አመራር ተግባራት ውስጥ የተለያዩ የጋራ የሆነ
የአሰራር ስታንዳርድ ያላቸው የሥራ መደብ
መጠሪያዎች ይገኛሉ፡፡
• አስፈላጊ በሆነ ጊዜም በተለያዩ የስራ መደብ
መጠሪያዎች ውስጥ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን በቀላሉ
ለመሙላት እንዲሁም ተጨማሪ ባለሙያዎችን
ለመጠየቅም አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
1. የአደጋ መቆጣጠር አዛዥ ሚናና ኃላፊነት
በአደጋ መቆጣጠር አዛዡ ተልዕኮ/ስራ የሚሰጠው ባለሙያ ስልጣንና
ኃላፊነት ሊኖረው ይገባል፣
አጠቃላይ አደጋውን የመምራት ኃላፊነት አለበት፣
የአደጋ ምላሽ ባለሙያዎችን ደህንነት ማረጋገጥ፣
የህዝቡን እና የአካባቢውን ጤናና ደህንነት ማስጠበቅ፣
ለውስጥ እና ለውጪ ባለድርሻ አካላት መረጃ ማቅረብ፣
ከሌሎች ተቋማት ጋር ግንኙነት መፍጠር፣
2. በትዕዛዝ ዕዝ ስር ያለ የሰው ሀይል ሀላፊነት
ሀ.የህዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ኃላፊነቶች፣
የመረጃ ስርጭትን በተመለከተ የአደጋ መቆጣጠር አዛዡን
ያማክራል፣
ለማንኛውም የመረጃ ፍላጎት ተጠሪ ሆኖ ያገለግላል፣
ለውጭ እና ለውስጥ ተገልጋዮች የመረጃ አገልግሎት ይሰጣል፣
የመረጃዎችን ከዕቅድ የሥራ ዘርፍ፣ ከህብረተሰቡ፣ ከሚዲያው
እና ከሌሎች ይወስዳል፣
ከሌሎች የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ጋር በትብብር ይሰራል፣
ለ.የደህንነት(safety) ኦፊሰር ኃላፊነቶች
 የአደጋ ሠራተኞችን ደህንነት ያረጋግጣል፣

 በደህንነት (safety) ጉዳይ የአደጋ መቆጣጠር አዛዡን


ያማክራል፣
 የአደጋ ሠራተኞችን የአደጋ ስጋት ለመቀነስ ይሰራል፣
ሐ.የአገናኝ(Liaison) ኦፊሰር
 ከተባባሪና አጋዥ ተቋማት መረጃዎችን የማሰባሰብ ስራ ይሰራል፣

 በአደጋ ስራው የተሳተፉ ተቋማትን ከዕዝ ሰንሰለቱ ውጪ በሆነ


መልኩ ያስተባብራል፣
 አጭር መግለጫ እንዲሁም ለጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፣
3.የጠቅላላ መምሪያ የሰው ሀይል ሀላፊነት
ይህ መምሪያ የኦፕሬሽን ፣ ዕቅድ፣ ግብዓት አቅርቦት፣ ፋይናንስና
አስተዳደር የሥራ ዘርፍ ዋና ሹሞችን የያዘ ሲሆን ቀጥታ
ተጠሪነቱም ለአደጋ መቆጣጠር አዛዥ ነው፡፡
ሀ.የኦፕሬሽን የሥራ ዘርፍ ዋና ሹም ኃላፊነት
የኦፕሬሽን የሥራ ዘርፍን ያደራጃል፤ ይመራል፡፡
የአደጋ መቆጣጠር ስትራቴጂዎቸንና ስልቶችን ይነድፋል፣
እንዲተገበር ያደርጋል፡፡
ከሌሎች በዕዝ እና በጠቅላላ መምሪያ ውስጥ ከሚገኙ
አባላት ጋር በስልታዊ አተገባበር ዙሪያ በቅርበት ይሰራል፡፡
ለ.የዕቅድ ዘርፍ ሹም ኃላፊነት
መረጃዎችን እና ሚስጢራዊ መረጃዎችን ይሰበስባል፣
ይተነትናል፣ ያሰራጫል፣
የዕቅድ ሂደቱን ይከታተላል፣ ይመራል፣

የአደጋ ጊዜ ዕቅድን በአንድ ላይ ያደራጃል፣

የቴክኒካል ባለሙያዎችን ተግባራት ይከታተላል፣ ይመራል፣

ከአደጋ መቆጣጠር አዛዡ እና ከጠቅላላ መምሪያ አባላት ጋር

በቅርብ ግንኙነት ይሰራል፣


ሐ.የግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ሹም ኃላፊነት
ለአደጋ መቆጣጠር ስራ የሚጠቅሙ ግብዓቶችን እና
አገልግሎቶችን እንዲቀርብ ያደርጋል፣
በአደጋ ጊዜ ዕቅድ ውስጥ ከግብዓት አቅርቦት አኳያ
የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ያቅዳል፣ እንዲካተትም ያደርጋል፣
ለአደጋ መቆጣጠር ተግባር የሚያገለግሉ ግብዓቶችን እና
አገልግሎቶች ለማቅረብ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ይኮናተራል፣
መ.የፋይናንስና አስተዳደር ዘርፍ ሹም ኃላፊነት
የባለሙያዎችን እና የቋሚ ግብዓቶችን የሥራ ሰዓት

ይቆጣጠራል፣
የይገባኛል ጥያቄዎችን ያደራጃል፣ የአፈፃፀም ሂደታቸውን

ይከታተላል፣
ወጪዎችን ይከታተላል፣ የተደረሰበትን የወጪ ደረጃ

ያሳስባል፣
2.4

የአደጋ መቆጣጠር ፋሲሊቲዎች
አደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስፍራ፡- አደጋ መቆጣጠር አዛዡ የአደጋዎች አጠቃላይ ሁኔታ
የሚከታተልበት ቦታ ነው፡፡
የመጠባበቂያ ቦታ፡- ለስራ ዝግጁ የሆኑ ግብዓቶች ትዕዛዝ የሚጠባበቁበት ቦታ ነው፡፡

ዋና የመቀመጫ ቦታ፡- ለአደጋ መቆጣጠር የሚያስፈልጉ የግብዓት አቅርቦት ተግባራት

በዋናነት የሚከናወኑበትና አስተዳደራዊ ጉዳዮች የሚፈፀሙትበት ስፍራ ነው፡፡


ካምፕ፡- ከስራ ውጪ የሆኑ ግብዓቶች የሚያርፉበት ቦታ ነው፡፡

የሄሊኮብተር ማረፊያ፡- ሄሊኮፕተር ማንቀሳቀስ በሚያስፈልግበት ጊዜ ለማረፊያና

ለመነሻ የምንጠቀምበት ቦታ ነው፡፡


የአመዕስ ዞን
2.5 የአደጋ ሥራ ዕቅድ
በአደጋ ሥራ ዕቅድ ውስጥ የአደጋ መቆጣጠር አዛዡ የተቀመጡ የአንድ ኦፕሬሽናል
ጊዜ ዓላማና ግብ እንዲሁም የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ስትራቴጂዎች ከአፈፃፀም
ስልቶቻቸው ጋር በግልፅ መቀመጥ አለባቸው፡፡
የአደጋውን ሁኔታ የሚያሳይ የመረጃ ፍሰት እና ስርጭትን በተመለከተ በዕቅዱ
ውስጥ መካተት አለበት፡፡ በዚህም መሰረት በእያንዳንዱ ኦፕሬሽናል ክፍለ
ጊዜ/ሺፍት ዕቅዱ የሚጨመሩ ጉዳዮችን በድጋሜ በመዳሰስ ማካተት ይኖርበታል፡፡
አንድ ዕቅድ ለአንድ ኦፕሬሽናል ጊዜ የሚያገለግል መሆን አለበት፡፡
ማንኛውም የአደጋ እቅድ የሚከተሉትን ነጥቦች
የያዘ መሆን አለበት ፡-
የአደጋ መቆጣጠር ዓላማውን የሚገልፅ

መፈፀም ያለባቸውን ዝርዝር ተግባራት የሚያሳይ

ኦፕሬሽናል ጊዜውን በጊዜ ገደብ የሚወስን መሆን

ያለበት ሲሆን እንደአደጋው ተጨባጭ ሁኔታም


ዕቅዱ የቃል ወይም የፅሁፍ ሊሆን ይችላል፡፡
በተጨማሪም የአደጋ ሥራ ዕቅዱ የሚከተሉትን ጥያቄዎች
የሚመልስ መሆን አለበት፡-
ምንድን ነው መስራት የምንፈልገው?
መጠባበቂያችን የት ነው የምናደርገው?
መቼ ነው የምንሰራው?
በማን ነው የሚሰራው?
ተግባቦታችን/ግንኙነታችን እንዴት ነው?
ችግር ሲያጋጥመን እንዴት እንፈታዋለን?
የመሳሰሉትን ጥያቄዎች የሚመልስ መሆን ይኖርበታል፡፡
3. የአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት ተግባቦት

በአደጋ መቆጣጠር ዕዝ ስርዓት ውስጥ የተግባቦት


ወሳኝ እና የጀርባ አጥንት ነው፡፡
 የተግባቦት ስታንዳርዱን የጠበቀና የጋራ የሆኑ
ቃላቶችን በመጠቀም ይኖርብናል
 የሚያደናግሩ ወይም ቶሎ ለመረዳት
የሚያስቸግሩ ቃላቶች መጠቀም አይመከርም
የሬዲዪ ወይም የስልክ አጠቃቀም ቅደም
ተከተሎችን መከተል፣
በግንኙነት ወቅት ግልፅና ቀላል ቋንቋ መጠቀም፣
ሬዲዮ እና ስልክን ወሳኝ ለሆኑ ጉዳዮች ብቻ
መጠቀም፣
4. የአደጋ ስራ ቁጥጥር
ይህ ተግባር፡-
ባለሙያዎች በአግባቡ እየሰሩ መሆኑን፣

የተመደበ ሀብትን ለመከታተል፣

ባለሙያዎችን ለስራ ለማዘጋጀት፣

አደጋ ያጋጠማቸውን ባለሙያዎች ለመለየት


ከአደጋ ቦታው መውጣት/መመለስ ያለባቸውን
ግብዓትችና ባለሙያዎች ለመለየት፣ እና
በአደጋ መቆጣጠር ተግባር የተሳተፈውን የአደፈጋ
ሰራተኛ ለመበተን ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡
5.የመጀመሪያ የአደጋ ስራ
መግለጫ/ማስገንዘቢያ/ማብራሪያ
መግለጫ/ማብራሪያ ለአደጋ ስራ አመራር ጠቃሚ መሳሪያ ነው፡፡
መግለጫ/ማብራሪያ ረጅም ጊዜ የሚወስድ መሆን የለበትም፡፡
 ባለሙያዎች ከተሰጣቸው ስራ አንፃር ግልፅ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ
ጥያቄዎችን በማንሳት በአጭሩ ሊብራራላቸው ይገባል፡፡
ማንኛውም በአመዕስ ውስጥ የሚሳተፍ ባለሙያ ወይም አመራር
ስለተሰጠው ስራ ማብራሪያ ሳያገኝ ወደ ስራ መግባት የለበትም፡፡
የስራ ማብራሪያዎችየሚከተሉት ጉዳዮች ላይ
ትኩረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡
የአደጋውን ሁኔታ
ግልፅ የሆነ የሥራ ተግባርና ኃላፊነት
የስራ አጋሮች እነማን እንደሆኑ
የስራ ቦታ/ስፍራ
ተጨማሪ አቅርቦት፣ አገልግሎቶች እና ባለሙያዎች
እንዴት ማግኘት እንደሚቻል፣
የኦፕሬሽን ክፍለ ጊዜ/ሺፍት
የደህንነት ቅደም ተከተል አተገባበር እና የግል
መከላከያ መሳሪያዎችን በተመለከተ መሆን
ይኖርበታል፡፡
6. የአደጋ መቆጣጠር አወጣጥ/አበታተን/
ይህ ማለት አደጋ መቆጣጠር ስራን በማጠናቀቃቸው
ምክንያት የማያስፈልጉ ግብኣቶችን እና ባለሙያዎችን ወደ
ነበሩበት ቦታ ወይም የሥራ ክፍል መመለስ ነው፡፡

የአደጋ መቆጣጠር አበታተን ዕቅድ የሚከተሉትን የሥራ


ጫናዎች ታሰቢ በማድረግ ወይም ግምት ውስጥ በማስገባት
ሊዘጋጅ ይችላል፡፡
የስራ ኃላፊነት እና የአደጋ መቆጣጠር አበታትን ታሳቢዎች

የህዝብ ግንኙነት ኦፊሰር

የተለያዩ መረጃዎች የማደራጀትና የማቀናጀት፣ ለሚዲያና


ለህብረተሰቡ መግለጫ የመስጠት ተግባር መቀነሱ
ከተረጋገጠ የህዝብ ግንኙነት ኦፊሰሩ ከአደጋ መቆጣጠር
ስራ እንዲወጣ ማድረግ ይቻላል፡፡
የደህንነት ኦፊሰር

የስልታዊ ኦፕሬሽን ስራ እየቀነሰ ከመጣ፣ የደህንነት ኦፊሰር


መኖሩ አስፈላጊ ካልሆነ፣ እንዲሁም የድጋሜ የስራ
ማብራሪያ ተግባራት ላይ ካላስፈለገ ከስርዓቱ እንዲወጣ
ይደረጋል፡፡
አገናኝ ኦፊሰር
የተባባሪና የዕርዳታ ሰጪ ተቋማት ሚና እየቀነሰ
ከመጣ የአገናኝ ኦፊሰሩ ሚና አነስተኛ ስለሚሆን
ከቦታው እንዲወጣ ማድረግ ይቻላል፡፡
የኦፕሬሽን ዘርፍ
የኦፕሬሽን ዘርፍ ሹሙ ድጋፍ ሰጪ ክፍሎችን
ማለትም ምክትሉን እና የመጠባበቂያ ቦታ ኃላፊውን
ሚናቸውን በማየት ከስራው እንዲወጡ ሊያደርግ
ይችላል፡፡
የዕቅድ ዘርፍ

የአደጋ መቆጣጠር ስራው እየተጠናቀቀ በሚሄድበት ወቅት


የስራ ውጥረት የሚያይለው በዘርፉ በሚገኘው የመረጃዎች
ማደራጃና የአደጋ መቆጣጠር አወጣጥ ክፍል ይሆናል፡፡
በመሆኑም ይህ ክፍል የአደጋ መቆጣጠር አወጣጥ ዕቅድ
በማዘጋጀት እንዲተገበር ክትትል ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም
በአደጋ መቆጣጠር ስራው የተከናወኑ፣ ውሳኔ የሰጠባቸውን
መረጃዎች የማደራጀት ተግባር ያከናውናል፡፡
የግብዓት አቅርቦት ዘርፍ
የአቅርቦት ክፍል እና የፋሲሊቲ ክፍል አደጋው በቁጥጥር ስር
ከዋለ በኋላ የሥራ ጫና የሚበዛባቸው ክፍሎች ናቸው፡፡
የግብዓቶችን ዝርዝር ማዘጋጀት፣ መሳሪያዎችን ለእድሳት
የማዘጋጀት፣ ያለቁ፣ የተጎዱ፣ የጠፉ ግብዓቶችን የመተካት
ተግባር የአቅርቦት ክፍል ኃላፊነት ይሆናል፡፡
የተለያዩ የተደራጁ ፋሲሊቲዎችን ማለትም የአደጋ ዕዝ
ስፍራ፣ ዋና የመቀመጫ ስፍራ፣ የመሳሰሉትን የመበተን
ተግባር የፋሲሊቲ ማደራጃ ክፍል ይሆናል፡፡
የፋይናንስና የአስተዳደር ዘርፍ

የአደጋ መቆጣጠር ስራው ከተጠናቀቀም በኋላ


የፋይናንስና አስተዳደር ተግባራት ሊቀጥሉ
ይችላሉ፡፡
አመሰግናለሁ!!!

You might also like