Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 8

ግሩም አባት ነህ

ግሩም አባት ነህ የምትራራ


የምትረዳኝ በመከራ
ባንተ ድኝያለሁ ነጻ ወጥቻለሁ
ተመስገን ኢየሱሰ እልሃለሁ
1. ቀርቦ የምያጽናና በጠፋበት
መካራው በዝቶ ባየለበት
ጌታዬ ነበርክ በዚያ ሥፍራ
እያጽናናኸኝ እንዳልፈራ
ግሩም አባት ነህ………
2.በሌለበት የሚያረካ ነገር
በዚያ በረሃ ደረቅ ምድር
የሕይወት ተስፋ ሆነህልኝ
ከዓለት ውሃ አፈለቅክልኝ
ግሩም አባት ነህ………
3.አውሎ ንፋሱ እየነፈሰ
ማዕበሉም እያተራመሰ
ወደ እኔ የደረሰ ሲመስለኝ
ለሕይወቴ ስሰጋ ሳለሁኝ
ግሩም አባት ነህ………
4.ግራ ቀኝን ባይ ዙሪያው አጥር
ሆኖብኝ ነበር ኑሮ በምድር
መውጫ ከሌለው ከዝግ ቦታ
አንተ አወጣኸኝ የኔ ጌታ
ግሩም አባት ነህ………
5.ለአስጨናቂው እጅ ሳልገዛ
ስለበዛልኝ የአንተ እገዛ
ወጥችያለሁኝ ቅጥሩ ፈርሶ
የወሰንከውም ጊዜ ደርሶ
ግሩም አባት ነህ………
ግሩም አባት ነህ

You might also like