Onion Production

You might also like

Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 41

የሽንኩርት አመራረት ዘዴ

በአብዱልጀሊል አመኑ

ታህሳስ/2016
2

ጠቀሜታ

 የሽንኩርት ጠቀሜታዎች
 ካረቦሃይድሬት፣ ቫይታሚን (ኤ፣ ቢ፣ ሲ)፣ ካልሲየምና ፎስፎረስ የሚባሉ ማዕድናትን
በውስጡ የያዘ ነው፡፡
 በተጨማሪም የተለየ ጣዕም ስላለው በቅመምነት ባህሪው ለሾርባ፣ ለወጥ
ማጠፈጫነትና ለመሳሰሉት አገልግሎት ይውላል፡፡

2
3

ዝሪያ(ድቃላ ያልሆኑ)
ዝርያ የኩርቱሽፋን የአንድ ምርት ለመስጠት ምርታማነትበኩ/ል
ተ.ቁ ቀለም ኮረትአማካይ የሚወስድበት /ሄ/ር(በምርምርማሳ)
ክብደት ጊዜ/ቀናት/
/ግራም/

1 ናፊድ ቫዮሌት ቀይ 102 99 600 -650

2 ሮባፍ(Robaf) ደማቅቀይ 85-95 100120 320

3 ናፊስ ቀይ 100-130 90-100 400

4 ናሲክሬድ ቀይ 80-85 90-100 300


5 አዳማሬድ ደማቅቀይ 65-80 120-135 350
6 መልካም ቀይ 85-100 130-142 400
7 ሬድክሮውል ደብዛዛቀይ 60-70 130-140 300

8 ቦምቤሬድ ደብዛዛቀይ 70-80 135-145 300


3
4
ዝሪያ(ዲቃላ የሆኑ)

ዝርያ አስመጪ ካምፓኒ ምርታማነት የመድረሻ ልዩ ባህሪያትን


ተ.ቁ
(በኩ/ሄ) ጊዜ /ቀናት/
ኔፕቱን ግሪን ላይን ቀይ ኮረት መልክ ያለው
1 ትሬድንግ 620 -

ጥሩ ድህረ-ምርት ቆይታ፣ነጣ ያለ ቀይ ኮረት መልክ፣ለውጭ ገበያ


የሚውል
636 90-105
2 ሲቫን

3 ጀምበር መኮቡ 750 90 ወጥ ኮረት ያለው፣ቀማቅ ቀይ ኮረት መልክ ያለው

4 ሬድ ኪንግ ማርቆስ 582 90-100 ቀማቅ ቀይ ኮረት መልክ ያለው፣ ፈጥኖ ደራሽ

5 ሩሴት ግሪን ላይን 655 80 በጣም ቶሎ ደራሽና ጥሩ ድህረ-ምርት ቆይታ ያለው


ትሬድንግ

6 አዳ ግሪን ላይን 697 70 በጣም ቶሎ ደራሽና ለሰላድ የሚወደድ፣ወርቃማ የኮረት መልክ

7 ስዊት ካሮሊን ኢምፓክት 251 105 በቀላሉ አበባ አያወጣም፣


ሙንዲያል

4
5

የቀጠለ...

Red Creole
Bombay Red

5
6

የቀጠለ...

Neptune

6
7
ሽንኩርት ለማምረት ተስማሚ ሁኔታዎች

Ø ከባህር በላይ - ከ700 - 2200 ከባሕር ወለል በላይ


የሙቀት መጠን- የቀን አማካይ የሙ ቀት ከ18- 24
የማታ አማካይ ሙቀት ከ 10-15 ቢሆን
በተለይ ቆላማ በሆኑ ሥፍራዎች የቀዝቃዛ ወቅትን ተከትሎ ቢመረት ጥሩ ምርት ይሰጣል፡፡

የዝናብ መጠን
በዕድገቱ ወቅት ከ 350-550 ሚ.ሜ. ውሃ ያስፈልጋል፡፡
ከዝናብ ይልቅ የፈረንጅ ቀይ ሽንኩርትን በመስኖ ቢመረት በተለይ ፐርፕል ብሎች የተባለውን በሽታ
ለመከላከል ያስችላል፡፡
ሆኖም ግን በዝናብ ወቅት ለማምረት ሲፈለግ በተለይም የምርት ስብሰባው ወቅት ደረቅ መሆኑ መረጋገጥ
መቻል አለበት፡፡ 7
8
ሽንኩርት ለማምረት ተስማሚ ሁኔታዎች

የአፈር አይነት - በተለያዩ የአፈር አይነቶች መመረት ይችላል፣ ቢሆንም ከፍተኛ ምርት የሚሰጠዉ
በሚያጠነፍፍና የአፈር ኮምጣጤነት ደረጃዉ ከ 6-6.8 ፒኤች በሆነ አፈር ላይ ነዉ፡፡
ቀላል ሆኖ አሸዋማ ቀመስ /sandy loam/ አፈር አይነት ይስማማዋል፡፡

8
9

የመድብ/ የማሳ ዝግጅት

 የፈረንጅ ቀይ ሽንኩረትን በለሰለሰ ማሳ ላይ መስመር አውጥቶ በቀጥታ በመዝራት ማምረት ይቻላል፡፡


 ነገር ግን ይህ ከፍተኛ የአረም፣ በሽታና ተባይ ቁጥጥርን ስለሚፈልግ መደብ ላይ ዘርቶ ችግኝ በማፍላት ወደ
ዋናው የመትከያ ማሳ በማዛመት ማምረቱ የተሻለ ነው
 የሚዘገጃው መደብ ስፋቱ 1 ሜ ርዝመቱ ከ 5-10 ሜ መሆን አለበት፡፡
 መደቦቹ ላይ አግድም በ የ15 ሳ.ሜ. ርቀት መስመሮችን ማዘጋጀት፣

9
10

የመድብ/ የማሳ ዝግጅት

 የሽንኩርት ዘር ለማብቀል የተለያ እንክብካቤና ጥንቃቄን የሚጠይቅ ስለሆነ የተመረጠው


ቦታ አፈር ለም ካልሆነ
 2 እጅ አፈር፣
 1 እጅ ፍግ/ኮምፓስት/ እና
 1 እጅ አሸዋ በማድረግ ደባልቆ መደቡን ማዘገጃት ያስፈልጋል፡፡

 መደቦቹ ላይ አግድም በየ15 ሳ.ሜ. ርቀት መስመሮችን ማዘገጃት፣


 ዘሩን በጥንቃቄ በወጣዉ መስመር ላይ በመበተን አፈር በስሱ መመለስና ሣር ማልበስ
 ዉሃን ወዲያዉ ማጠጣት

 ለአንድ ሄ/ር የሚያስፈልገው የመደብ ብዛት /1 ሜ x 5 ሜ/ ስፋት ያላቸው 112 መደቦች


በ560 ካሬ ሜትር ስፋት ቦታ ላይ ማዘጋጃት ይቻላል፡፡

10
11
ዘር መዝራት

 ዲቃላ ላልሆኑ ዝርያዎች ከ6.5-7.5 ኪ.ግ ዘር በሄ/ርያስፈልጋል፡፡


ዲቃላ ዝርያ ከሆነ ከ3-4 ኪሎ ግራም ዘር በሄ/ር ያስፈልጋል፡፡
 ዘር ሲዘራ በተዘገጃው መደብ ላይ እስከ 0.5 ሴ.ሜ. በማራራቅ መዝረትና በስሱ አፈር
በማልበስና በላዩ ላይ ጉዝጓዝ በማንጠፍ ውሃ ማጠጣት ያስፈልጋል፡፡

11
12

የማሳ ዝግጅት

 መሬቱን በደረቅ ወቅት 20-30 ሳ.ሜ ጠለቅ አድርጎ ከ2-3 ጊዜ ደጋግሞ በማረስ፣ ማለስለስና
ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡
ሶስት ዓመታት የሽንኩርት ቤተሰብ (የአበሻ ቀይ ሽንኩርት፣ ባሮ፣ ነጭ ሽንኩርት ወዘተ) የሆኑ ሰብሎች
ያልተመረቱበት መሆን አለበት፡፡

12
ችግኝን ማለማመድ

የተዘገጃው ችግኝ ለማዛመት አንድ ሳምንት ሲቀረው በፊት ሲሰጠዉ የነበረውን ውሀ መጠን በመቀነስና
የማጠጫ ቀናቶቹንም በማራራቅ ማላመድ ይቻላል፡፡

 ይህም ከመደብ ወደ ማሳ ሲዛወር የሚያገጥመውን ተጽዕኖ እንዲቋቋም ይረዳዋል፡፡


ችግኙ ከተዘራ ከ45-55 ቀናት ሲሆነዉ ወደ መትከያ ማሳ ማዛመት ያስፈልጋል
ሲተከል አፈሩን በሥሩ ዙሪያ በሚገባ መጠቅጠቅ ችግኞቹ እንዲፀድቁ ይረዳል

13
አተካከል

 የችግኙ ዕድሜ ከ40-50 ቀን ሲሞለው ወይም ከ3-4 እውነተኛ ቅጠል ሲያወጣ ወደ ዋናው የመትከያ ማሳ
ማዛመት ይቻላል፡፡

ቀይ ሽንኩርት 20 ሳ.ሜ. ስፋት ባለዉ መደብ ሁለቱ ጠርዞች (በመስመሮች

መካከል በ20 ሳ.ሜ ርቀት) እና በተክሎች መካከል ዲቃላ ላልሆኑት ዝርያዎች 5

ሳ.ሜ. እንዲሁም ለዲቃላ ዝርያዎች 7 ሳ.ሜ. አራርቆ መትከል ያስፈልጋል፡፡

 በመደቦቹ መካከል ያለዉ የዉሃ ቦይ 40 ሳ.ሜ. ስፋት ይኖረዋል፡፡

14
የቀጠለ...

1 15
የመስኖ ዉሀ አጠቃቀም

 የመስኖ ዉሃ ከወንዝ፣ ከምንጭ፣ ከጉድጓድ፣ ከሃይቅና ከልዩ ልዩ ማጠራቀሚያዎች ማግኘት ይቻላል

የመስኖ ዉሀ አጠቃቅም እንደስነ-ምህዳሩ ሁኔታና የአፈሩ ዓይነት ይለያል፡፡

መጀመሪያ ችግኙ ሲዛወር መሬቱ በሚገባ ዉሃ መጠጣት አለበት፡፡

 የሽንኩርት ተክል ስሩ አጭር ስለሆነ መደቡ በቀላሉ ሊናድ ስለሚችል ዉሃ ሲናጠጣ ጥንቃቄ ማድረግ
አለበት

 ቀጥሎም በሞቃት አየርና በቀላል አፈር በየ5 ቀኑና በጥቁር አፈርና ቀዝቃዛ አካባቢዎች በየሳምንቱ የመስኖ
ዉሀ ማጠጣት ያስፈልጋል፡፡

16
አረምና ኩትኳቶ

ኩትኳቶና የአፈር ማስታቀፍ ተግባር የሚከናወነው በሁለት ዙር ሆኖ


 የመጀመሪያው መዳበሪያ በሚደረግበት ወቅትና

ሁለተኛው ደግሞ ማበብ ሳይጀምር ይከናወናል፡፡

ሽንኩርትን ከተዛመተ ከሁለት ሳምንት በኋለ ቢያንስ ሁለት ጊዜ ከኩትኳቶ አቀነጅቶ ማረም
ያስፈልጋል፡፡

የአረም ሥራ በተለይ በደረቅ ወቅት ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡

17
ማዳበሪያ አጠቃቀም
ሽንኩርት ከፍተኛ ንጥረ-ነገር ከምፈልጉት ዉስጥ አንዱ ነዉ

ሽንኩርት በበቂ ሁኔታ ማዳበሪያ ካልተጠቀምን በቂ ምርት አይሰጥም

በቂ ማዳበሪያ ( ለምሳሌ ናይትሮጅን) ሲያገኝ ቅጠሉ የፋፋና የተሻለ ኩርት ለማዘጋጀት ይጠቅመዋል

ማዳበሪያ በጨመርን ቁጥር የበልቡ ስፋትና ምርት እየጨመረ ይሄዳል

ናይትሮጅንና ብስባሽ አብሮ ስጨመር ምርቱ ይጨምራል

ዳፕ 200 ኪ.ግ/ሄር ችግኙ ከመዛመቱ በፊት ማሳዉ ላይ መጨመር

ዩሪያ 100 ከ.ግ/ሄ ግማሹ በተከላ ወቅት የቀረዉ ደግሞ ከ45 ቀን ቦሃላ ቢጨመር የሻለ ይሆናል

18
ሰብል ጥበቃ

አንጥረኛ (Thrips)

 በከፍተኛ ደረጃ በመከሰት የሚታወቀው የሽንኩርት ዝርያ በሆኑት ቀይ የሃበሻና የፈረንጅ


ሽንኩርትና እንዲሁም ነጭ ሽንኩርት ላይ ነው
 በጣም ትንሽ ነፍሳት ተባይ ብትሆንም በዓይን የምትታይ ናት

 ተክሉን የሚያጠቁትም በዕጭ የዕድገት ደረጃና ጉልምስ ዕድሜ ላይ የሚገኙት ሲሆኑ


 እነርሱም የቅጠሉን የውጭ ክፍል በመብላትና በቅጠሉ ውስጥ የሚገኘውን ፈሳሽ በመምጠጥ የተክሉ ቅጠል
እንዲጠወልግ ወይም እንዲጨማደድ ያደርጉታል፡፡
 በዚህ ነፍሳት ተባይ የተጎዳ ተክል ቅጠሉ ነሀስ (siliver) ቀለም፤ ትንንሽ የሆኑ ቡናማ ነጠብጣቦች እንዲሁም
የቅጠሉ የላይኛው ክፍል ጫፍ ቡናማ ቀለም ይኖረዋል፡፡
 ·

1 19
የቀጠለ...

 የዚህ ተባይ ጉዳት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ የተክሉ ቅጠል ሙሉ በሙሉ እንዲጠወልግ፤ በልቡ
(bulb) ትንሽና መጥፎ ቅርፅ (ቅርፅ አልባ) ሊያደርገው ይችላል
 በወቅቱም የመከላከል እርምጃ ካልተወሰደ የምርት ጥፋቱ 50% በላይ ሊሆን ይችላል፡፡

20
መከላከያ/መቆጣጠሪያ መንገዶች

በማሳ አያያዝ
 የሽንኩርት ተክልን በአንድ ማሳ ላይ ደጋግሞ (በተከታታይ) መትከልን/ ማልማትን ማስወገድ (አንጥረኛ መልሶ
እንደይከሰት ለማድረግ)፤
 በሽንኩርት ማሳ ውስጥና በማሳው ዙሪያ የሚገኙትን አረሞች (የማይፈለጉ ተክሎችን ማስወገድ (ለአንጥረኛ
መጠለያነት ስለሚያገለግሉ)፤
 ትክከለኛውን የአተካከል ርቀትና የማዳበሪያ መጠን መጠቀም
 ቢጫ፤ ሰማያዊ እና ነጭ የሚያጣብቁ ትራፖችን መጠቀም፤

 በኬሚካል መጠቀም
 እንደ ሌሎች የአትክልት ተባዮች የሽንኩርት አንጥረኛ ተባዮችን (thrips) ለመከላከል የተመዘገቡ ፀረ-ተባይ ኬሚካሎች
በርካታ ቢሆኑም የተመዘገቡ ፀረተባይ ኬሚካሎችን አፈራርቆ ባለመጠቀም ምክንያት የሚጠበቀዉን ዉጤት ማግኘት
አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል
 ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችን አፈራርቆ መጠቀም
2 21
22
የቀጠለ....
የንጠረ ነገሩ ወይንም የጋራ የሚመደብበት ክፍል የንግድ ስሞች (ገበያ ላይ ያሉ)
ስም
Profenofos OP Ajanta 72% EC (W/V); Danefos 72%
EC;Golbe 72% EC; Prior 72 EC; Proof
72EC; Comax 72EC; Seamless 720 EC;
Girgit-Plus
Lambda-Cyhalothrin Pyrethroid Lamog 5% EC; Locslay 5% EC; Triger
5 EC
Imidaclopprid Neonicotinoid Fighter, Imidacel
Acetamipride + Neonicotinoide + Cutter 112 EC
emamectin benzoate Avermectin
Thiamethoxam + Neonicotinoid + Eforia 247 SC
Lambda-Cyhalothrin Pyrethroid
Neem Natural product Nimbicidine
Lufenuron + profenfos Benzoylurea + OP Curador 55EC
Spinetoram Spinosyns Radiant 120 SC

22
23

የበሽታ ቁጥጥር

ፐርፕል ብሎች (Purple blotch)


ይህ በሽታ በየትኛውም የሽንኩርት አብቃይ አካባቢና በሁሉም የሽንኩርት ማምረቻ ወቅቶች በስፋት የሚከሰትና ከፍተኛ
ጉዳት የሚያስከትል በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡

 የበሽታው ምልክቶች
 በሽታው ሲጀምር በቅጠሉ ላይ ቡናማ ወይም ፐርፕል ቀለም ያለው ጠባሳ ያሳያል፡፡
 ለበሽታው መስፋፋት አመቺ ሁኔታዎች (ከፍተኛ ዝናብና የአፈር እርጥበት) ሲኖርና ዝርያዎቹ በቀላሉ
የሚጠቁ ከሆነ ቅጠሎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊደርቁና ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡

23
24

የቀጠለ...

24
25

የበሽታው መከላከያ ዘዴዎች

 በአንፃራዊ በሽታውን በመቌቌም የታወቁ የሽንኩርት ዝርያዎች መዝራት


 ከበሽታ ነጻ የሆነና ምንጩ የታወቀ የሽንኩርት ዘር መጠቀም
 ሰብልን ማፈራረቅ (የአሊየም ቤተሰብ ባልሆኑ ሰብሎች)
 የመስኖ ውኃን በአግባቡና መጥኖ መጠቀምና የዝናብ ውኃን በአግባቡ ማጠንፈፍ
 የተመዘገቡ ፀረ-ፈንገስ ኬሚካሎችን መጠቀም፡ ለምሳሌ Mancozeb 50% WP at 3 kg/ha እና
Ridomil Gold MZ 68% WP at 2.5 kg/ha

25
26

የኮረት አበስብስ (Bulb rot) በሽታ

 ይህ በሽታ ቀይ ሽንኩርትን፤ የአበሻ ሽንኩርትንና ነጭ ሽንኩርትን በማጥቃትና ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ


ይታወቃል፡፡ ይህን በሽታ የሚያስከትለው ፈንገስ በአፈር ውስጥ ለረጅም ጊዜ (ከ 3-5 ዓመት) ሊቆይ
ይችላል፡፡
 ይህ ባህሪው በሽታውን በቀላሉ ለመከላከል አስቸጋሪ ያደርገዋል
 በሽታው በዋናነት የሚያጠቃው የሽንኩርቱን ኮረት ሲሆን ከመሬት በላይም በቅጠሉ ላይ የመጠውለግና
የመድረቅ ምልክቶችን ያሳያል፡፡
 ኮረቱ ላይ ነጭ ጥጥ መሳይ የፈንገስ እድገት ከዚያም በመቀጠል ጥቁር የጎመን ዘር የሚመስሉ ክብ የፈንገሱ
አካላት ይታያሉ፡፡
 ከፍተኛ የዝናብ መጠንና የአፈር እርጥበት በሚኖርበት ጊዜ በሽታው በቀላሉ በመስፋፋት ኮረቱን በሙሉ
በማበስበስና ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፡፡

26
27

የቀጠለ...

በኮረት አበስብስ በሽታ የተጠቃ ቀይ ሽንኩርት

27
28

የመከላከያ ዘዴዎች

 ሰብልን ማፈራረቅ (ሽንኩርት መሰል ባልሆኑ ሰብሎች /non Alliums)


 የሽንኩርት ማሳን ከአረም የጸዳ ማድረግ
 ኮረቱ ከመተከሉ በፊት በተመዘገቡ ፀረ-ፈንገስ ኬሚካሎች መለወስ

28
29
እስቴምፋይለም ብላት
(stemphylium blight (Stemphylium vesicarium)

 ይህ በሽታ ከ 2001 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ በዋና ዋና የሽንኩርት አብቃይ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ
መከሰቱ ተመዝግቧል፡፡
 በሽታው እሰከ 95% የስርጭት መጠን ያለው መሆኑ ታይቷል።
 የሽንኩርት ቅጠሎችን በማጥቃት ከፍተኛ የሆነ የምርት ቅነሳ ያደርሳል፡፡

 የበሽታው ምልክቶች
 በሽታው ሲጀምር ነጣ ያሉ ቢጫማ ትናንሽ ዉኃ አዘል ጠበሳዎች ይታያሉ
 ጠባሳዎች እየሰፉ እና እያደጉ ስሄዱ ጠባሳዎቹ ተቀላቅሎ የተቃጠለ ቅጠል በማስመሰል በቅጠሎቹ ላይ ከፍተኛ
ጥቃት ያደርሳሉ
 በዚህ በሽታ ምክንያት የሚከሰተው በሽታ ከፕርፕል ብሎች በሽታ ጋር ተመሳሳይ ምልክት ያለው ሲሆን አንዱ
ከአንዱ መለየት አዳጋች ያደርገዋል

29
30
የቀጠለ...

ሰቲምፋይለም ብላይት ምልከት

30
31

የመከላከያ ዘዴዎች

 ተመዘገቡ ፀረ-ፈንገስ ኬሚካሎችን መርጨት ለምሳሌ Mancozeb 50% WP at 3 kg/ha እና


Ridomil Gold MZ 68% WP at 2.5 kg/ha የበሽታውን የዕድገት ሂደትን ይከላከላል፡፡
 ረዘም ያለ ሰብል ፈረቃ ስርአትን መከተል፣ የማሳውን የእርጥበት ይዘት የተስተካከለ ማድረግ እና ተገቢ
የአተካከል ርቀትን መከተል ናቸው፡፡

31
32

ዳውኒ ሚልዲው (Downy mildew)

 ይህ በሽታ በአብዛኛው የሚያጠቃው የሽንኩርት ቅጠልን ሲሆን ከፍተኛ ዝናብና የአፈር እርጥበት ለበሽታው
መስፋፋት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ይታወቃሉ፡፡
 በወይናደጋና ደጋማ አካባቢዎች በሽታው በስፋት ይታያል፡፡ የሀበሻ ሽንኩርትንም በከፍተኛ ደረጃ ሊያጠቃ
ይችላል፡፡
 የበሽታው ምልክቶች
በሽታው በአብዛኛው የሚያጠቃው ቅጠሉን ሲሆን የመጀመሪያ ምልክ በቅጠሉ ላይ ግራጫ ወይም አመድ
መሳይ የፈንገሱ ብናኝ መታየት ነው፡፡
ዝናብና ከፍተኛ የአፈር እርጥበት በሚኖርበት ወቅት በቀላሉ በመስፋፋት የሽንኩርቱን ቅጠል ሙሉ በሙሉ
የማቃጠልና ከፍተኛ የምርት ቅነሳን በማስከተል ይታወቃል፡፡

32
33

በዳውኒ ሚልዲው የተጠቃ ቀይ ሽንኩርት

33
34
የመከላከያ ዘዴዎች

 ሰብልን ማፈራረቅ (ሽንኩርት መሰል ባልሆኑ ሰብሎች /non Allium crop species
 የመስኖ ውኃን መጥኖ መጠቀም
 የሽንኩርት ማሳን ከአረም የነጻ ማድረግ
 የተመዘገቡ ፀረ-ፈንገስ ኬሚካሎችን መርጨት ለምሳሌ Mancozeb 50% WP at 3 kg/ha እና
Ridomil Gold MZ 68% WP at 2.5 kg/ha የመሳሰሉትን መጠቀም።

34
35

የምርት አሰባሰብና ድህረምርት አያያዝ

 ሽንኩርት መድረሱ የሚታወቀው እንደ የዝርያው ከተተከለበት ቀን ጀምሮ ለምርት ማድረሻ ቀኑን ቆጥሮ
በማገናዘብ፣ አብዛኛው ቅጠሉ ተቆልምሞ ወደ መሬት ሲያዘነብል፣ወይም ከ 50-75 በመቶ ያህል ቅጠሉ ወደ
መሬት ሲወድቅ ነው፡፡
 ሽንኩርት መድረሱ ሲታወቅ በደረቃማና ጸሐያማ ቀን መነቀል ያለበት ሲሆን የተነቀለው ሽንኩርት ከነቅጠሉ
ማሳ ላይ በጸሐይ በማጠውለግ የኮረቱ የላይኛው ሽፋን እንዲጠነክር ማድረግ ይቻላል
 የጠወለገው ሽንኩርት ከአንገቱ ከ1-2 ሳ.ሜ ከፍ ብሎ ቅጠሉን በማስወገድ ጫፉ እንዲዘጋ በደረቅ ወለል ወይም
ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ አልጋ ላይ በመዘረር እንዲደርቅ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

 ወደ መጋዘንም ይሁን ወደ ገበያ በሚጓጓዝበት ሰዓት በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸው ኮረቶች ተለይቶ ከምርቱ
ውስጥ ማውጣት አለባቸው፡፡
35
36

ማጠገግ

 ሽንኩርትን ከተነቀለ በኋለ ከነቅጠሉ በጸሐይ ውስጥ ከ 5-7 ቀናት በመስክ ውስጥ በማቆየትና
ከተቆረጠም በኋላ አንገቱ እስከሚዘጋ በደረቅና ነፋሻማ ስፍራ ላይ በማጠውለግ ማዳን /curing/
ይባላል፡፡
 የሽንኩርትን ኮረት ውጫዊ ሽፋን /ቆዳ/ ቀስ በቀስ በማድረቅ ከውስጥ በትነት የሚወጣውን ውሃና ምግብ
እንዳይባክን ስለሚረዳ የድህረ-ምርት ብክነትን በመቀነስ አምራቹን ውጤታማ ያደርጋል፡፡
 የማጠንከር ተግባር በመጋዘን ውስጥም የታመቀ ብርሃንና አየር በሚገባበት መጋዘን ውስጥ ከእንጨት
በተሰራ ሼልፍ ላይ በስሱ በመዘረር በየጊዜው በማናፈስና የተጎዱትን ለይቶ በማውጣት ጤናማ ኮረቶችን
ብቻ በማቆየት ሊከናወን ይችላል፡፡
 በዚህ መሠረት ሽንኩርትን ከ 2-3 ሳምንት ማቆየት ይቻላል፡፡

36
37
የቀጠለ....

 ከዚህም በተጨማሪ ከማሳ ደርቆ የተሰበሰባውን ሽንኩርት ቢያንስ 25 ኪ.ግ. ሊይዝ በሚችል
ከቃጫ የተሰራ ጆንያ ተሞልቶ በደረቅ ነፋሻማ መጋዘን ውስጥ እስከ 3 ሜትር ባለው ከፍታ
በመደርደር ማከማቸት ይቻላል፡፡

 ሽንኩርት በሚከማችበት መጋዘን ውስጥ መኖር ያለበት የሙቀት መጠን ወደ ዜሮ ዲ.ሴ. የተጠጋና
የአካባቢ የእርጥበት መጠንም ከ 70 በመቶ መብለጥ የለበትም፡፡

37
የቀጠለ....

እንደጎጆ ሆኖ በተለያየ ስፋት መሥራት ይቻላል

 ከማንኛዉም እንጨት ማዘጋጀት ይቻላል

 ለሽንኩርት ማስቀመጫ እንደቆጥ ነገር ከመሬት ከፍ ብሎ አግድም ይዘጋጃል

 ከቆጡ ሥር አየር ማስገቢያ ሲኖረዉ ከላይ ከግድግዳዉ ላይ ሙቀት የሚወጣበት


መስኮት ነገር አለዉ

 ዋና ጥቅሙ ሙቀትን መቆጣጠር ነዉ

38
39
ጎንጉኖ መስቀል

39
40
በኬሻ ማስቀመጥ

40

You might also like