Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 30

በስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ

ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት


የስጋ መጥበሻ /ሮዝመሪ/ ልማት በተቋምና በአ/አደር የተገኘ ተሞክሮ

2014 ወራቤ
ሮዝሜሪ (Rosemary)?

• በሳይንሳዊ አጠራር ------Rosemary officinalis L.

• በሀገራችን-----------ጥብስ ቅጠል ወይም አዝመሪኖ

• በእድገት ባህሪው-------ቁጥቋጦ ሰብሎች ቤተሰብ

• በእድገት ዘመኑ---------ቋሚ ሰብል


Rosemary Origin and Distribution?
 የስጋ መጠበሻ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘዉ
ከሜዲትራንያ አከባቢ ነዉ፣

 ሮዝሜሪ ከ500 BC በሮማዊያን፣ ጥንታዊት


ግሪክ እና በመሳሰሉት ሀገሮች በባህላዊ ምግብ
እና መድሃኒት ዝግጅት እንድሁም በሌሎች
ማህበራዊ ግልጋሎት አገልግሎት ላይ ይዉል
እንደ ነበር ጥናቶች ያሳያሉ፣
ዋና ዋና የሮዝሜሪ አምራች ሀገራት

• አዉሮፓ --------ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋል

• አፍሪካ -----------ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ኬንያ

በኢትዮጵያም ይመረታል
1. እርጥብ ቅጠል---------ለአሳ፣ ለስጋ መጥበሻነት፤ ቲማቲም ፣ ሾርባ፣ ለስልስ ማጣፈጫነት…

2. ደረቅ ቅጠል----------- ለባልትና (ሽሮ፣ በርበሬ) ዝግጅት…

3. ዘይት -------------ለኢንደስትሪ ግብዓትነት (የምግብ፣ ኮስሞቲክስ፣ መድሃኒት…)


ሮዝመሪን ለማምረት የሚያስፈልጉ ምቹ የአካባቢ ሁኔታዎች

• አዝመሪኖ በተፈጥሮ የሞቃታማ አካባቢ ተክል ሲሆን በእርጥበት አዘልና ቀዝቃዛ አካባቢዎች ላይም በጥሩ ሁኔታ ሊያድግና ምርት
ሊሰጥ ይችላል፣

• የቀን ሙቄት ከ20-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ

• አማካይ ዓመታዊ ዝናብ 500 ሚ.ሜትር

• አፈሩ፡-ለም፣ ዉሃ የማያቁር፣ ጣዕመ አፈር 5.5-8.0

• ከፍታ 1500-3000 ሜ.
የሮዝሜሪ ምርት

20-28 ቶን ቅጠል ምርት/ሄክታር


110-250 ኪ/ግ መዓዛማ ዘይት/ሄክታር

• ከ100 ኪሎ ግራም ርጥብ ምርት ከ20-25 ኪሎ ግራም ደረቅ


ወ/ገ/ግ/ም/ማዕከል ሪፖርት
ከዚህ አኳያ ዞናችን ምቹ የሆነ ስነ-ምህዳርና ሰፊ ሊለማ የሚችል መሬት ባለቤት እንደመሆኑ በስጋ መጥበሻ
ልማት የሚሸፈነውን ማሳ ለማስፋትና የምርታማነት ደረጃውንም ማሳደግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳለ
ያመለክታሉ ፡፡በዞናችን እስካሁን 1897 ሄ/ር ነባር በሮዝመሪ ማሳ የተሸፈነ ሲሆን በዘንድሮ 666ሄ/ር ታቅዶ
ይለማል,2563ሄ/ር ይዳርሳል፡፡ካሉን ወረዳዎች ልማቱ ያለባቸው ወ/ከ/አስ/ ፣ስልጢ፤ ፣ምስ/አዘ/በርበሬ፤አ/ውሪሮ
፣ሁልባራግ፤እና ምእራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳዎች ላይ አ/አደር ሮዝመሪ በማልማት ተጠቃሚ እየሆነ ቢመጣም
በዘርፈ የተለያየ ውስንነቶች ይታያል ፡፡
 በባለሙያውና በአምራች አ/አደሩ ዘንድ የግንዛቤና ክህሎት ማነስ
 የድህረ-ምርት አያያዝ
 የገበያ ትስስር ችግር ዋና ዋናዎቹ ናቸው
ስለሆነም በቀጣይ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀምና በዘርፋ ያለውን የፓኬጅና ከግብይት ጋር
ተያይዞ የሚታየውን ችግር መቅረፍ ከተቻለ ቀደም ሲል ወደ ልማት ያልገባና በሌሎች ሰብሎች
ውጤታማ የሆነ መሬትን ጭምር በማልማት በስጋ መጥበሻ ተክል ልማት የአርሶ አደሩን የገቢና የኑሮ
ደረጃ ማሻሻል እንደሚቻል በዞናችን በተለይ በወራቤ ከተ/አስ/ በዘርፉ ልማት የሚሳተፉ አ/አደሮችና
ት/ት ተቋማት ማየት ይቻላል፡፡
በመሆኑም እነዚህን አ/አደሮችና ተቋማት(ት/ቤት) የፈጸሙበትን አግባብና የተገኘውን ውጤት
ተሞክሮ እንደመነሻ በመጠቀም ወደ ሁሉም አከባቢዎች የማስፋት ስራ በማከናወን አ/አደሩንና
ሀገርቷን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ተሞክሮቻቸውን እንደሚከተለው ማቅረብ ተችሏል ፡፡
ዓላማ
 የተጀመሩ መልካም ስራዎችን ወደ ሌሎች አከባቢዎች በማስፋት ከዘርፉ የተሻለ ገቢ በማግኘት የአ/አደሩን
ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ከድህነት ማላቀቅና የሀገራችንን የውጭ ምንዛሪ ከፍ ማድረግ ነው
 የተራቆቱ አከባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ በማስቻልና ወደ ልማት በማስገባት ተጨማሪ ሀብት ለመፍጠር
 በአነስተኛ መሬት በትንሽ ወጪ ብዙ ሀብት ለማግኘት
. የሮዝመሪ መልካም ተሚክሮ
በአ/አደር ደረጃ የተገኘ ምርጥ ተሞክሮ
የአ/አደር ስም---- ሙሀመድ ከማል
• ወረዳ ----------ወራቤ ከተማ አስተዳዳር
• ቀበሌ -----------አንሸቤሶ
• የመንደር ስም------ ዲያጢስ ልማት ቡድን
• የመሬት መጠን--- 0.25ሄ/ር
• የተገኘ ውጤት --- ከ10ኩ/ል 65,000 ብር ገቢ
ስነ-ምህዳር
ወይና ደጋ እና 2150ሜትር ከፍታ
 የአፈር አይነት ቀይ አሸዋ ቀመስ
ውጤት የተገኘበት አግባብ (አፈጻጸም
የማሳው ቅድመ ታሪክ
• ለምነቱ እጅግ እየተዳከመ የመጣና በየመዓቱ ስንዴና በቆሎ በማልማት
ዝቅተኛ ምርት የሚገኝበት መሬት ነበር፡፡
ማሳ ዝግጅትና ተከላ
• በአካባቢው በተለመደው የመትከያ ሁኔታ ከ30-40ሳ/ ጥልቀት ቦይ
በበሬ በማረስና በማውጣት በወጣው ቦይ ውስጥ እስከ 50ሳ/ በተክል
መካከል እና ከ60 ሳ/ሜትር በቦይ መካከል በማድረግ ይተከላል
• እስከ ከ8000 በላይ ግንጣዮች በክረምት ወራት በመስመር
ተክሎዋል፡፡
የቴ/ጂ አጠቃቅም
 ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተፈጥሮ ማዳበሪያ በመጨመር ምርታማነቱን ማሻሻል መቻሉና ለሰው ሰራሽ
በማዳበሪያ የወጣው ወጪ አለመኖሩ
አረምና ኩትኳቶ
 የአረም ችግር በሚኖርበት ወቅትና የበልግ ዝናብ ሲገባና የመኽር ዝናብ ሲወጣ መደበኛወን
ኩትኩዋቶ በሰው ሀይል በመኮትኮት እና በእጅ በማረም አረምን ከማሳ ውስጥ የማስወገድ ስራ
ሰርቷል፡፡
ምርት አሰባሰብ
 አ/አደር ምርት ለመሰብሰብ ሲደርስ በሰራተኛ በማሳጨድ እንዲሰበሰብ በማድረግና ሸራ ላይ
ተወቅቶ ለገበያ ማቅረብ ችሏል
የአ/አደሩ ማሳ በከፊል
የወጪና ገቢ ስሌት
የወጪና ገቢ ስሌት 1ኛ ዙር( 2012/13)
ወጪ;
 በ2011/12 ዓ.ም. ለእርሻ ዝግጅት 5000 ብር ፣ ችግኝ ግዢ 5000 ብር ፣ ተከላ 3500 ብር ፣ ኩትካቶ 2000 ብር ፣ አጨዳ ውቅያ
ጥቅጣቆና ወደ ገበያ ማጓጓዝ 5000 ብር ሲሆን ወጪ ድምር 20,500 ብር
ገቢ
 የተገኘ ምርት 8ኩ/ል ፣ የወቅቱ የገበያ ዋጋ 1ኪ/ግ = 55 ብር ሲሆን 8ኩ/ል ወይም 800ኪ/ግ×55 ብር = 44,000 ብር
የተጣራ ትርፍ ፤- የተገኘ ገቢ -- የወጣ ወጪ / 44000-20,500/= 23,500 ብር ነው፡፡

በ2ኛ ዙር በ2013/14
ወጪ፡-
 በ2013/14 ዓ.ም. አረምና ኩትኳቶ 3500 ብር፣ አጨዳ ውቅያ ጥቅጣቆና ወደ ገበያ ማጓጓዝ 7000 ብር ሲሆን ወጪ ድምር 10,500
ብር
ገቢ
 በ2013/14 ም.ዘመን ; የተገኘ ምርት 10ኩ/ል ፣ የወቅቱ የገበያ ዋጋ 1ኪ/ግ = 65 ብር ሲሆን 10ኩ/ል ወይም 1000ኪ/ግ×65 ብር =
65,000 ብር
የተጣራ ትርፍ ፤- የተገኘ ገቢ -- የወጣ ወጪ / 65000-10,500/= 54,500 ብር ነው፡፡

ይህም በሄ/ር ስሰላ በዓመት 218 ሺህ ብር የሚገኝ በመሆኑ አዋጪነቱ በጣም የላቀ ነው
ከዚህ ተሞክሮ የተወሰደ

 በአነስተኛ መሬት በትንሽ ወጪ ብዙ ሀብት ማግኘት


 የተራቆቱና ለምነታቸው የደከሙ መሬቶች ላይ ሮዝመሪ በማምረት
አ/አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ
2.በተቋም
የተቋም ደረጃ የተገኘ
ስም አያንቶ ት/ቤት፤- ስጋ መጥበሻ ልማት ተሞክሮ
ምርጥ ስራ የገባው ከ2007 ዓ/ም ጀምሮ ሲሆን በመጀመሪያ አመት በ0.5 ሄ/ር ላይ
የጀመረው ስራ እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ የመሬቱን ሽፋን 15 ሄ/ር በማድረስ ከ6 ዙር በላይ ምርት በመሸጥ ተጠቃሚ መሆን ችሏል፡፡
 በ2014 ዓ.ም ምርት ከሚሰጥ ከ13 ሄ/ር መሬት ላይ በለማ የሮዝመሪ ምርት ሸያጭ 1014000 ብር ገቢ ማግኘት ችሏል
ተሞክሮ የተገኘበት አካባቢ
 ስልጤ ዞን
 ወረዳ ወራቤ ከተማ አስተዳዳር
 ቀበሌ አንሸቤሶ
 የመንደር ስም፤ ቆረት ልማት ቡድን
ስነ-ምህዳር

 ወይና ደጋ እና ከባህር ጠለል በላይ 2150ትር ከፍታ


 የአፈር አይነት ቀይ አሸዋ ቀመስ
የማሳው ቅድመ ታሪክ፤-
የተከናወኑ ስራዎች
 ለምነቱ እጅግ እየተዳከመ የመጣና በየመዓቱ ስንዴና በቆሎ በማልማት ዝቅተኛ ምርት የሚገኝበት መሬት
ነበር፡፡

የተከላ ወቅት፤-
 ዝናብ ባለበት ወቅት እና በቂ እርጥበት በሚኖርበት ወቅት የሚተከል ሲሆን በአካባቢው እየተለመደ
የመጣው በክረምት ወራት በሰኔ ወር ነው፡፡
 ሮዝመሪ በት/ቤቱ ከ2007 ዓ/ም ጀምሮ 0.5ሄ/ር መልማት የጀመረ ሲሆን ሽፋን እሰከ 2014 ዓ/ም 15ሄ/ር
ደርሷል፤፤ ከዚህ ውስጥ 13ሄ/ር ነባርና ምርት ለመሰጠት የደረሰ ነው፤
የአተካከል ሁኔታ
 በበሬ በማረስና ቦይ በማውጣት በወጣው ቦይ ውስጥ እስከ 50 ሳ/ሜትር በተክል መካከል እና 60ሳ/ሜትር በቦይ መካከል
በማድረግ የመትከያ ጉድጓድ በመቆፈር ተተክሏ
 በዚህ መሰረት ት/ቤቱ ባለማው 15 ሄ/ር መሬት ከ490ሺህ በላይ ግንጣዮች እንዲኖር በማድረግ ተተክሏል፡፡
የቴክኖሎጂ አጠቃቅም
 ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ት/ቤቱ በኩትኩዋቶና ብስባሽ በመጠቀም የሚያለማው በመሆኑ ለማዳበሪያ ያወጣው
ወጪ የለም
አረምና ኩትካቶ
 የአረም ችግር በሚኖርበት በተለይ ዝናብ በሚጥልበት ጊዜ በበልግና በመኸር ወቅት በሰው ሀይል በመኮትኮት
እና በእጅ በማረም ወይም በጥንቃቄ በበሬ እንደ በቆሎ በመሸልሸል አረምን የማስወገድ ስራ ተሰርቷል፡፡
ምርት አሰባሰብ
 ሮዝመሪ ቋሚ ቅመማ ቅመም ሰብል ሲሆን ከተተከለ ከ1 አመት ጀምሮ በአከባበው በየአመቱ ምርቱ
ለመሰብሰብ ይደርሳል፡፡
 የምርት አሰባሰቡ ሂደት በማሳው ላይ እያለ ተገምቶ በኮንትራት ስለተሸጠ ምርት የማሰባሰብ ስራው
በነጋዴዎች ተሰርቷል፡፡
የአያንቶ ት/ቤት ማሳ በከፊል
የወጣ ወጪ
 የወጪና
የወጪና (በ2013/14
ገቢገቢ ስሌት ምርት ዘመን)
 የወጣ ወጪ; በ2013/14 ም/ዘመን
 ለእንክብካቤ ስራዎች 54000
 ጠቅላላ የወጣ ወጪ ድምር 54000 ብር

 የተገኘ ገቢ በ2014 ዓ/ም


 የተገኘ ምርት 494 ኩ/ል
 የወቅቱ የ 13 ሄ/ር ማሳ የስጋ መጥበሻ ምርት የተሸጠበት የጨረታ ብር = 1014000 ብር
 የ 1 ሄ/ር መሬት የምርታማነት መጠን 38 ኩ/ል
 ከ 13 ሄ/ር በስጋ መጥበሻ ከለማ መሬት የተገኘ ገቢ = 1014000 ብር
 የተገኘ ገቢ ; የሽያጭ ብር ሲቀነስ የወጣ ወጭ (1014000-54000)
 የተገኘ የተጣራ ትርፍ = 960000 ብር ነው፡፡
ከዚህ ተሞክሮ የተወሰደ ትምህርት
 ት/ቤቱ ለምነቱ የደከመውን ሰፊ መሬት ሮዝመሪን
በማልማት የሀብት ምንጭ ማድረግ መቻሉ
 በተገኘው ሀብት ት/ቤቱ ከ1 ሚ/ን በላይ ላይብረሪ እያስገነባ
መሆኑ
 መሬት በስፋት ያላቸው ተቋማት ሮዝመሪን በማልማት ጥሪት
መገንባት እንደሚቻል

በተቋሙ ቅጥር ግቢ የላይብረሪ ግንባታ


እንደ ወ/ከ/አስተዳደር ጥቅል ሲታይ /ለውጡ የመጣበት ሂደት/
 እስከ2007 የሮዝመሪ ልማት 10-15ሄ/ር በ46 አ/አደሮች እየለማ የነበረ ሲሆን በወቅቱ የ1ኪ.ግ ዋጋ 8-11ብር
ነበርና አ/አደሮች በዋጋ ተስፋ ቆርጠው ልንራብ ነው ብለው ተክሉን መንቀል ጀምረው ነበር፡፡ምክንያቱ በሦስት ዋና
ዋና ችግሮች
1. አ/አደሩ የገበያ መረጃ የሌላቸውና ትስስር አለመፈጠሩ
2. አከባቢ ላይ ያሉ ደላሎች አድማ አድርገው በዝቅተኛ ዋጋ ከአ/አደሩ በመግዛት ለማ/ገበያ በማቅረብ ነገዴው ብቻ
መጠቀሙ
3. የመንግስት መዋቅር ጠጋ ብሎ አለመደገፍ ናቸው
ከላይ የተዘረዘሩ ችግሮች በልማቱና በግብይቱ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለመለየት በተደረገው የደሰሳ ጥናት ወቅት የተለዩ
ችግሮች ነበሩ፡፡ በዚህ ጥናት የዞንና የወ/ገ/ግ/ም/ማዕከል ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት
ተደርጎዋል፡፡
በዚሁ መሰረት በገበያ መረጃና ትስስር፤ በኤክስቴሽን አተገባበርና በሌሎች ተግባራት ላይ ለአመራር፤ለባለሙያና
ለአ/አደር የግንዛቤ ስራ በመስራትና የባለሙያ ድጋፍ በተወሰነ መልኩ እየተሻሻለ በመምጣቱ የ1ኪ.ግ ዋጋ 11 ብር--
20-28ብር በመግባቱ የልማት ሽፋኑም ምርቱም እየጨመረ መጣ፡፡ይህም በመንግስት ደረጃም ትኩረት እያገኘ
በመምጣቱ በ2012 የክልሉ ቡ/ቅ/ቅ/ ባለስልጣን የመስክ ጉብኝት እንዲካሄድ በማድረግ ልማቱ እንዲነቃቃ
አድርጎታል፡፡
የቀጠለ…
ልማቱና ምርቱ እጨመረ በመምጣቱ የክህሎትና የገበያ ትስስር ችግሮች እየተፈጠሩ በመምጣታቸው የክልሉ
ቡ/ቅ/ቅ/ ባለስልጣን የክህሎት ክፍተትን ለመሙላት በ2013 ስልጠና የሰጠ ሲሆን የገበያ ችግሩን ለመፍታት ዞኑ
በ2013 ማህበር እንዲደራጅ በማድረጉ የአከባቢ ነጋዴዎች ምርቱ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይሄድባቸው የዋጋ ጭማሪ
በማድረግ 1ኪ.ግ ከ30-45 ብር መግዛት ጀመሩ፡፡አሁን ላይ 65-74 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ አጠቃላይ ሽፋኑ 675 ሄ/ር በ903 አ/አደሮች በ3 ቀበሌዎች እየለማ ሲሆን ከዚህ ውስጥ
435ሄ/ር 735 አ/አደሮች የተሞክሮ ባለቤት በሆነችዋ በአንሸቤሶ ቀበሌ እየለማ ይገኛል፡፡ይህም ከአጠቃላይ
ሽፋኑ 64.4% እና ከአጠቃላይ ተሳታፊ አ/አደሮች 81.4% ድርሻ ትይዛለች ፡፡
በዚህች ቀበሌ 115 አ/አደሮች 1ሄ/ርና በላይ፤ 125 አ/አደሮች 0.75ሄ/ር ፤180አ/አደሮች 0.5ሄ/ር፤ 248
አ/አደሮች 0.25ሄ/ር እና 67 አ/አደሮች ከ0.25ሄ/ር በታች ያላቸው ናቸው ፡፡0.25ሄ/ርና በላይ ያላቸው
አ/አደሮች በምርቱ ተጠቃሚ እየሆኑ መሆኑን ያሳያል ይህም ከ65ሺ--300ሺህ ብር የሚያገኙ ሲሆን ከሚያለሙ
አ/አደሮች ከ91% በላይ ተጠቃሚ ናቸው፡፡ዘንድሮ ከተመረተው 13920ኩ/ል ከ93% በላይ ለገበያ ቀርቦዋል፡፡
በዘንደሮ ዓመት 195ሄ/ር በአዲስ መሬት በማልማት ሽፋኑን 630 ሄ/ር ለማድረስ ታቅዶዋል፡፡
የዞናችን የቅ/ቅመም ምርት አቅርቦት
 የቅ/ቅመም ምርት አቅርቦት፤- 15197 ቶን ለማቅረብ ታቅዶ 14153 ቶን(93%) ለማ/ገበያ የቀረበ ነው፡፡
 በሮዝመሪ ምርት ዘንድሮ ከተመረተውና በክምችት ከነበረው ጨምሮ 31600ኩ/ል ለማ/ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ 30435ኩ/ል(96%)
የቀረበ ሲሆን ከዚህ ውስጥ እስካሁን ባለው 3200ኩ/ል ኤክስፖርት ተደርጎ 640ሺህ ዶላር ተገኝቶዋል፡፡450ኩ/ል ኤክስፖርት
ለማድረግ ውል ተገብቶዋል በሂደት ላይ ይገኛል፡፡

 ምርቱን ወስደው ኤክስፖርት የሚያደርጉ ላኪዎች


1. የህያ ሰዒድ
2. ገና Trading PLC…..
ለቅ/ቅመም ምርት ምቹ ሁኔታዎች
 ያለን ስነ-ምህዳርአመቺ መሆኑ
 በአለም ላይ ተፈላጊነታቸው እጨመረ መምጣቱ
 ቅመማ ቅመም በመዳረሻ ሀገራት ሲታይ ኢንዶኔዥያ በመጠን 570 እና በገቢ 3.0455 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር
ህንድ በመጠን 2362.6 ቶን እና በገቢ 1.63406 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር፣አሜሪካ በመጠን 115.67557 ቶን
እና በገቢ 0.7605 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር አፈፃፀም በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡መዳረሻ
ሀገራቱ 46 ናቸው
 ከሚያስገኙት ጥቅም አንጻር በቀጣይ ጊዜያት የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸው
 የቅ/ቅመም ላኪዎች ቁጥራቸው እጨመረ መምጣት (256 ደርሰዋል)
 በዚህ ዘርፍ የሚሰራ ምርምር ተቆዋም ያለ መሆኑ(ወ/ገ/ግ/ም/ማዕከል)
ማነቆዎች

በአመራሩ፤በባለሙያውና በአምራች አ/አደሩ ዘንድ የግንዛቤና ክህሎት ማነስ

የድህረ-ምርት አያያዝ(የጥራት ጉድለት)

መረጃና የገበያ ትስስር ችግር ዋና ዋናዎቹ ናቸው


3.በበርበሬ ልማት ላንፍሮ
•የአ/አደሩ ስም --ከድር ዑመር  የገቢና ወጪ ስሌት
•ወረዳ--- ላንፍሮ ፤ ቀበሌ ----------ሻ/ጡፋ ፤ ወጪ፤-ለእርሻ፤ለግብዓትና ለእንክብካቤ ስራዎች ጠቅላላ
ል/ቡድን----- አጋም ላንፍሮ፤ ወጪ 5255 ብር ሲሆን
የቴክ/ጂ አጠቃቀሙንና የአግሮኖሚውን ስራ በተገቢው ገቢ፤- የተገኘ ምርት 5.4 ኩ/ል ሲሆን የአንድ
በመፈጸም ኩንታል ዋጋ 20000 ብር=108,000 ብር ተሸጦ
በ0.2ሄ/ር የተገኘ ምርት 5.4ኩ/ል በማግኘት 102745 ከወጪ ቀሪ 102745 ብር አገኙ
ብር ማግኘቱ
ከዚህ ተሞክሮ የተወሰደ ትምህርት
-የመሬት ልያታና የእርሻ ካላንደሩን በተገቢው መጠበቁ
-ጥራት ያለውን ዘር በራሱ በማዘጋጀትና በኬሚካል በማሻት ጠንካራ
ችግኝ በመትከሉ
-ማሳውን በዝናብ ወቅት በቅርበት ተከታትሎ እንክብካቤ ማድረጉ
ምርቱን በተገቢው በሻራ በማድረቁ የተሻለ ዋጋ ማግኘቱ
30

ያሾክራው

You might also like