Professional Documents
Culture Documents
Electronic Trading - Training Material - Revised
Electronic Trading - Training Material - Revised
2013 ዓ .ም.
የምርት ገበያዉ የህግ ማዕቀፍ
• የምርት ገበያዉ የህግ ማዕቀፍ እና አላማዎች
• የምርት ገበያዉ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 550/1999 የተቋቋመ
ድርጅት ነው፡፡
• የምርት ገበያዉ የተቋቋመዉ በአዋጁ አንቀጽ 6 ሥር የተዘረዘሩትን በርካታ ዓላማዎችን
መሠረት በማድረግ ሲሆን ከዓላማዎቹም ውስጥ፡
የአምራቾችን፣ የገዢዎችን፣ አቅራቢዎችንና ፍላጎት በማርካትና የኢትዮጵያ አነስተኛ አምራቾች
የገበያ ተሳትፎን በማሳደግ ዉጤታማ፣ ግልጽ አሠራርን የተከተለና በሥርዓት የሚመራ
የግብይት ሥርዓት መፍጠር፤
በምርት ገበያው የሚደረጉ ግብይቶች ካልተገደቡ ድርጊቶችና የህግ ጥሰቶች የራቁ በማድረግ
የምርት ገበያውን የግብይት ስረአት እና የግብይቶችን ጤናማነት ማስጠበቅ እንዲሁም
ተገበያዮች በምርት ገበያው ላይ በሚካሄዱ ግብይቶች ላይ እምነት እንዲኖራቸው ማድረግ፤
የምርት ደረጃ ምስክር ወረቀትንና ዋስትና ያለዉ የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ መሠረት በማድረግ
ግብይት ማካሄድ፤
ግዴታን ባለመወጣት የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመቀነስ በምርት ገበያዉ የሚከናወኑ
ግብይቶችን ክፍያና ርክክብ የመፈጸም፤ እና
ወቅታዊ የገበያ መረጃዎችን ለህዝቡ ማቅረብ የሚሉት ይገኙበታል ፡፡
• በምርት ገበያው የማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ 6 ዉስጥ የተቀመጡትን ዓላማዎች
ለመተግበር እንዲረዳ የምርት ገበያዉ አሰራር የሚመራበትን ዝርዝር ደንብ አዉጥቶ
በየጊዜው አስፈላጊው ማሻሻያ እየተደረገበት በሥራ ላይ ይገኛል፡፡
የምርት ገበያው ደንብ የምርት ገበያዉ ስራ አመራር፣ ስለምርት ገበያ አባልነት፣
ስለተገበያዮች፣ ስለማከማቻ መጋዘን፣ ክፍያና ርክክብ፣ የገበያ መረጃ ስርጭት፣
ስለዲሲፕሊን እና አፈጻጸም፣ ቁጥጥር እንዲሁም ሌሎች ከግብይት ጋር ተያያዥነት
ያላቸው ጉዳዮች የሚመሩበትን ዝርዝር ህግ አስቀምጧል፡፡
የግብይት ስርዓት
በምርት ገበያው የሚደረግ ግብይት ምርት ገበያው በሚወስነው አኳኋንና የጊዜ ሰሌዳ
መሠረት
በመገበያያ መድረክ ድምጽን በማስተጋባት ወይም
በኤሌክትሮኒክ ግብይት መድረክ ላይ ተወዳዳሪነትን በሚጋብዝ ሁኔታ ይካሄዳል፡፡
(አንቀጽ 5.1፣ 5.3)
የኤሌክትሮኒክ ግብይት ተርሚናል የሥራ ማከናወኛ መሣሪያ ተጠቃሚን መለየት (አንቀጽ 5.3.3)
እያንዳንዱ ተጠቃሚ የራሱ መለያ ቁጥር ይኖረዋል፡፡ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ተወካይ እና የራሱን መመሪያ
የሚያስገባ ደንበኛ የተጠቃሚ መለያ ምዝገባ ሁልጊዜ የጸና እና ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ የአባሉ ኃላፊነት
ነው፡፡
እያንዳንዱ የኤሌክትሮኒክ የግብይት ተወካይ ኤሌክትሮኒክ የግብይት
መድረኩን ለመጠቀም ልዩ መለያ ቁጥር እና የይለፍ ቃል (Password)
መጠቀም አለበት፡፡
የኤሌክትሮኒክ ግብይት ተወካይ ከተጠቃሚው ውጭ ሌላ ሰው የእሱን
መለያ ቁጥር እና የይለፍ ቃል (Password) ተጠቅሞ ትዕዛዝ ወይም
መመሪያ እንዲያስገባ መፍቀድ የለበትም፡፡
የኤሌክትሮኒክ ግብይት ተወካይ የሚጠቀምበትን የይለፍ ቃል (Password)
ለማንኛውም ሰው (ለምሳሌ ለስራ ባልደረባ ፣ ለቤተሰብ አባላት)
ማሳወቅ የለበትም፡፡
የኤሌክትሮኒክ ግብይት ተወካይ የሚጠቀምበትን የይለፍ ቃል (Password)
ሌሎች ሰዎች ሊያዩት በሚችሉበት ቦታ ማስቀመጥ የለበትም፡፡
የኤሌክትሮኒክ ግብይት ተወካይ የሚጠቀምበትን የይለፍ ቃል
(Password) ሌሎች ሰዎች አውቀውት ሊሆን ይችላል ብሎ ስጋት
ካደረበት ለግብይት ስርዓት ቁጥጥር ክፍል ለአባላት ሁኔታውን
በማሳወቅ የመለያ ቁጥሩን ማስቀየር አለበት ፡፡
የኤሌክትሮኒክ ግብይት ድጋፍ (አንቀጽ 5.3.4)
• የምርት ገበያው ኤሌክትሮኒክ የግብይት ስርዓት ቁጥጥር ክፍል ለአባላት እና
ኤሌክትሮኒክ የግብይት ተወካዮች ድጋፍ እና ለሚከሰቱ ችግሮችም መፍትሄ
ይሰጣል፡፡ ምርት ገበያው በተወሰነ ጊዜ ለዚሁ ጉዳይ በተመደበ ስልክ ወይም
በሌላ የኤሌክትሮኒክ መንገድ ድጋፍ ሊሰጥ ይችላል፡፡
የግብይት ደንቦች
ፋንተም ትዕዛዝ ወይም መመሪያ ማለት 1) የምርት ገበያው የግብይት ስርዓት በጉድለት
ወይም በብልሽት የገባው መረጃ (ለምሳሌ ያህል ውል፣ መጠን ወይም ዋጋ)
ከኤሌክትሮኒክ የግብይት ተወካይ እውቅና ውጭ በምርት ገበያው የግብይት
ስርዓት ወይም አገልግሎት ላይ በተከሰተ ጉድለት ወይም ብልሽት ምክንያት ሲቀየር
ነው::
•ትዕዛዝ ማስገባት
• በምርት ገበያው የኤሌክትሮኒክ ግብይት ማካሄድ የሚቻለው በተፈቀዱ
የኤሌትሮኒክስ ግብይት ስራ ማከናወኛ መሳሪያዎች አማካኝነት ብቻ ነው፡፡
• መመሪያ ወይም ትዕዛዝ ወደ ኤሌክትሮኒክ መገበያያ መድረክ ማስገባት የሚችለው
በምርት ገበያው የሚዘጋጀው የተጠቃሚ መለያ ቁጥር የተሰጠው ሰው ብቻ
ነው፡፡
• መመሪያ ወይም ትዕዛዝ ለማስገባት ቢያንስ የሚከተሉት መረጃዎች
ያስፈልጋሉ፡የተሰጠ መለያ ቁጥር፤የአባል መለያ ቁጥር፤ዋጋ፣ ብዛት፣ የግብይት
አይነት (የገዥ ወይም የሻጭ)፤ የሚጸናበት ጊዜ፤የቀርብበት ቦታ፤ እና የምርት
መረጃ ናቸው፡፡
የኤሌክትሮኒክ የግብይት ተወካይ የተቀበለው መመሪያ በቀጥታ ወደ
ኤሌክትሮኒክ የግብይት መድረክ ማስገባት የማይቻል ከሆነ መመሪያውን እና
የተመደበለትን ሂሳብ፣ ቀን፣ መመሪያው የተሰጠበትን ጊዜ ጨምሮ
የተሰጠውን መመሪያ በጽሁፍ መያዝ አለበት፡፡ መመሪያው መፈጸሚያው
ጊዜ ሲደርስ ወደ ኤሌክትሮኒክ የግብይት ስርዓት ውስጥ መግባት አለበት፡፡
• የግብይት ደንቦች
ማንኛውም አባል እና የግብይት ተወካይ ከሌላ ግለሰብ ጋር ባለው ቅርበት የተነሳ የተገለፁለትን
ትዕዛዞች ለሚመለከተው የምርት ገበያ ወይም ለባለስልጣን ሰራተኛ ካልሆነ በስተቀር መግለፅ
የለበትም፡፡
አባል ወይም የግብይት ተወካይ ከማንኛውም ትዕዛዝ/ መመሪያ ወይም ውል ጋር በተያያዘ ለሌላ
ሰው ወይም በሌላ ሰው ስም ሲሰራ ማታለል፣ በሀሰት ሪፓርት ማድረግ፣ ሆነ ብሎ ማጭበርበር፣
የራስን ጥቅም ማስቀደም ማስገደድ፣ አሳሳች መሆን፣ምርትን ከገበያ ማስወገድ፣ የተሳሳተ መረጃ
ማሰራጨት፣ የውስጥ አዋቂ መረጃ ተጠቅሞ ግብይት መፈጸም እና የምርት ተፈላጊነት ላይ
ሰውሰራሽ ተጽዕኖ ማድረግ የለበትም፡፡
በመገበያያ መድረኩ ላይ ተንቀሳቃሽ የመገናኛ መሣሪያዎችን (ለምሳሌ ስልክ) መያዝ
በምርት ገበያው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚደረጉ ግብይቶች በአግባቡ እንዳይከናወኑ ሊያደርግ
በሚችል ሁኔታ መንቀሳቀስ
ተገበያዮች ወደ ግብይት መድረክ ከገቡ በኃላ እርስ በራሳቸው መነጋገር ክልክል ነው(አንቀጽ 5.3.1.5
የደ.ቁ. 12/2012)
በምርት ገበያው የተዘጋጀ የመለያ ባጅ ሁል ጊዜ በግልፅ በሚታይ ቦታ ላይ ሳያንጠለጥል ወደ
መገበያያ መድረኩ መግባት የተከለከለ ነው። (አንቀጽ 5.3.1.3 (ሐ) የደ.ቁ. 12/2012)
አባላት፣ አባል ያልሆኑ ቀጥታ ተገበያዮች፣ የመድረክ ተወካዮች እንዲሁም
ደንበኞች የምርት ገበያውን ደንብ እና ሌሎች አግባብ ያላቸውን ህጎች በመጣስ
ጥፋቶችን ሲፈጽሙ ተፈጸሙ የተባሉት ጥፋቶች በምርት ገበያው የህግ
ማስከበሪያ መምሪያ ሰራተኞች ከተመረመሩ በሓላ የዲሲፕሊን እርምጃ
እንዲወሰድባቸው ለምርት ገበያው የግብይት አፈጻጸም ኮሚቴ ይቀርባሉ፡፡